እንዳንተ ፡ ማን ፡ ነው (Endante Man New) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x)
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ
በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ
ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ
ፍፁም ፡ ፈውስም ፡ በእጅህ ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ !
እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ
እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x)
ቤቴስ ፡ ምንድነው ?

የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ በአንተ ፡ አገኘሁ
ጌታ ፡ ተመስገን !
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆኗል
ከእኔ ፡ የሆነ ፡ የለም
አንተን ፡ የታመነ ፡ መች ፡ ወድቋል?
ዘለዓለም ፡ በጥላህ ፡ ይኖራል
በምትችለው ፡ በአንተ ፡ መመካት
ይሻላል ፣ ይጠቅማል ፡ መኩራራት !
ተነሣሁ ፡ ከአመድ ፡ ከትቢያ
ረዳኸኝ ፡ አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ !
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰልኝ !
ስምህን ፡ ለማክበር ፡ በቃሁኝ !

አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x)
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ
በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ
ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ
ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ !
እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ
እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x)
ቤቴስ ፡ ምንድነው ?

ቅጥርን ፡ ማዘለል ፣ ማበርታት ፡ ታውቃለህ
ለደካማው ፡ ኃይልን ፣ ብርታት ፡ ትሰጣለህ
ማለዳ ፣ ማለዳ ፡ ኃይልህን
በመከራ ፡ ጊዜ ፣ ማዳንህ
የማይዘነጋ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ
የየቀኑ ፡ ታላቅ ፡ ምክርህ

አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x)
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ
በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ
ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ
ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ !
እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ
እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x)
ቤቴስ ፡ ምንድነው ?

ያደረግኸው ፡ ለእኔ ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው
ጌታ ፡ ተመስገን !
የውለታህም ፡ ልክ ፡ ከምለው ፡ በላይ ፡ ነው
እጅህ ፡ የማይደክም ፡ ሁልጊዜ
ጽኑ ፡ መከታ ፡ ነህ ፡ ለነፍሴ
ማረፍ ፡ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
ዘወትር ፡ ስምህን ፡ ማክበር ፡ ነው

አዝ ፣ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ? (፬x)
በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ነህ
በሃዘንም ፡ ደስታ ፡ ነህ
ለታመመው ፡ መድሃኒት ፡ ነህ
ፍፁም ፡ ፈውሥም ፡ በእጅህ ፡ አለ
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ !
እስከዚህ ፡ ያደረስኸኝ
እኔ ፡ ማነኝ ? (፬x)
ቤቴስ ፡ ምንድነው ?