From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት?
ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት
ዝም ፡ ያሰኘለት?
ተራራ ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ጠላቴ ፡ ሲፎክር
የማይወድቅ ፡ መስሎት ፡ ሕይወቴን ፡ ሲያሸብር
በሰማይ ፡ የሚኖር ፡ አምላክ ፡ የሆነው
ከከፍታ ፡ አውርዶ ፡ በእግሬ ፡ ሥር ፡ ጣለው
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት?
ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት
ዝም ፡ ያሰኘለት?
ዘወትር ፡ ዕንቅፋትን ፡ በፊቴ ፡ ላይ ፡ ሲያኖር
ከበነዋል ፡ በቃ ! እያለ ፡ ሲፎክር
መብረቁን ፡ ልኮ ፡ ጌታ ፡ አወካቸው
ዳግም ፡ ላይነሱ ፡ በጥልቅ ፡ ጣላቸው
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት?
ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት
ዝም ፡ ያሰኘለት?
ነበረብኝ ፡ ብዙ ፡ ሸክም ፡ የሆነብኝ
ልቤንም ፡ አቅልጦት ፡ በጣም ፡ ያስጨነቀኝ
ጌታ ፡ ደርሶልኝ ፡ እኔን ፡ አስጥሎኛል
በቅዱሱ ፡ ማደሪያው ፡ እንዳርፍ ፡ እረድቶኛል
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት?
ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት
ዝም ፡ ያሰኘለት?
እንደዚህ ፡ እረድቶኝ ፡ ከጠላት ፡ ድኛለሁ
በማያልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ጸንቼ ፡ ቆሜያለሁ
ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ጌታ ፡ ይቀድመኛል
ስለሚዋጋልኝ ፡ ማክበር ፡ ይገባኛል
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት?
ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት
ዝም ፡ ያሰኘለት?
|