በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እታመናለሁ (Besemu Gulbet Etamenalehu) - ታደሰ ፡ መኩሪያ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ መኩሪያ
(Tadesse Mekuria)

Tadesse Mekuria 2.png


(2)

ታማኝ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
(Tamagn New Egziabhier)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ መኩሪያ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Mekuria)

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!

ገና ፡ ገና ፡ ከጅምሩ ፡ እኔን ፡ የመረጠኝ
የወደደኝ ፡ ያከበረኝ ፡ ሙሉ ፡ መብት ፡ የሰጠኝ
የከሳሼን ፡ ግንባር ፡ መቶ ፡ ፊቴ ፡ የዘረረው
የማመልከው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የሚኖረው

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!

ለነአብርሃም ፡ ለነይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ የሆናቸው
ሲድራቅ ፡ ሚሳቅ ፡ አብደናጐም ፡ ከእሣት ፡ ያወጣቸው
ለነጳውሎስ ፡ በደማስቆ ፡ ተገልጦ ፡ የታያቸው
እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሥልጣን ፡ በእጁ ፡ ያለው

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!

ኤልያስን ፡ የሚሰማ ፡ ሲጣራ ፡ በቅጽበት
ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ የሚመልስ ፡ በእሣት
አያሳፍር ፡ የበረታው ፡ በብርታቱ ፡ ታምኖ
ያኖረናል ፡ እየሠራ ፡ ጠላትን ፡ አባሮ

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!

እግዚአብሔር ፡ ዓብ ፡ ለአንድ ፡ ልጅ ፡ ሙሉ ፡ መብት ፡ የሰጠው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኛ ፡ ደግሞ ፡ እንዲሁ ፡ አሳለፈው
በደዌ ፡ አልጋ ፡ ለማቀቀው ፡ በእሥራት ፡ ለኖረው
መፍትሔ ፡ አለው ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ከእሥር ፡ ገላጋይ ፡ ነው

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!

የአምላኬ ፡ ሥም ፡ የጸና ፡ ነው ፣ ዛሬም ፡ ለዘለዓለም
የሚሠራ ፡ ኃይሉ ፣ ከቶ ፡ ጉልበቱ ፡ የማይደክም
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ያሻውን ፡ ያደርጋል
የሚከለክለው ፡ የለም ፣ በሥልጣን ፡ ይሠራል

አዝ፦ የእባቡን ፡ እራስ ፡ እቀጠቅጣለሁ!
ገና ፡ ሥራውን ፡ አፈራርሳለሁ!
በሥሙ ፡ ጉልበት ፡ እመታዋለሁ!
ዕቅድ ፡ ሃሣቡን ፡ አፈራርሳለሁ!
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ እመታዋለሁ!
ዘወትር ፡ ምክሩን ፡ አበላሻለሁ!