የታረደው ፡ በግ (Yetaredew Beg) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(1)

የታረደው ፡ በግ
(Yetaredew Beg)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 8:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

መጽሐፉን ፡ ትወስድ ፡ ዘንድ
ማኅተሞቹንም ፡ ትፈታ ፡ ዘንድ ፡ ይገባሃል
ታርደሃልና ፡ በደምህም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ከነገድ ፡ ሁሉ
ከቋንቋም ፡ ሁሉ ፡ ከወገንም ፡ ሁሉ
ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ሰዎችን ፡ ዋጅተህ
ለአምላካችን ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ይሆኑ ፡ ዘንድ ፡ አደረካቸው
በምድርም ፡ ላይ ፡ ይነግሳል ፡ እያሉ
አዲስን ፡ ቅኔ ፡ ይዘምራሉ [1]

መጽሐፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈቶ
ከሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ሰዎችን ፡ ዋጅቶ
ለአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ካህናት ፡ ሆንን
በበጉም ፡ ስራ ፡ ተመሰገንን

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

በሰማይና ፡ በምድርም ፡ ከምድርም ፡ በታች
በባሕርም ፡ ላይ ፡ ያለ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ
በእነርሱም ፡ ውስጥ ፡ ያለ ፡ ሁሉ
በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋናም
ኃይልም ፡ ከዘለዓለም ፡ እስከዘለዓለም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለበጉም ፡ ይሁን ፡ ሲሉ ፡ ሰማሁ [2]

በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ከምድርም ፡ በታች
በእነርሱም ፡ ውስጥ ፡ ያለን ፡ ፍጥረታት
ከዙፋኑ ፡ ፊት ፡ እንወድቃለን
ለበጉም ፡ ክብር ፡ እንዘምራለን

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

አየሁም ፡ በዙፋኑም ፡ በእንስስሶቹም ፡ በሽማግሌዎቹም ፡ ዙሪያ
የብዙ ፡ መላእክትን ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁ
ቁጥራቸውም ፡ አእላፋት ፡ ጊዜ ፡ አእላፋት ፡ እና ፡ ሺ ፡ ጊዜ ፡ ሺ ፡ ነበረ
በታላቅም ፡ ድምጽ ፡ የታረደው ፡ በግ ፡ ኃይልና ፡ ባለጠግነት ፡ ጠብብም ፡ ብርታትትም ፡ ክብርም ፡ ምሥጋናም
በረከትም ፡ ሊቀበል ፡ ይገባዋል ፡ አሉ [3]

እልፍ ፡ አእላፋት ፡ ብዙ ፡ መላእክት
ለታረደው ፡ በግ ፡ እሚሰግዱለት
እስከዘለዓለም ፡ ለሚኖር ፡ ጌታ
ቅኔ ፡ ሲቀኙ ፡ ጥዋትም ፡ ማታ

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

ከሽማግሌዎቹም ፡ አንዱ ፡ ተመልሶ
እንዚህ ፡ ነጩን ፡ ልብስ ፡ የለበሱ ፡ እነማን ፡ ናቸው
ከወዴትስ ፡ መጡ ፡ አለኝ
እኔም ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ ፡ አልኩት
አለኝም ፡ እነዚህ ፡ ከታላቁ ፡ መከራ ፡ የመጡ ፡ ናቸው
ልብሳቸውንም ፡ አጥበው ፡ በበጉ ፡ ደም ፡ አነጹ
ስለዚህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ አሉ
ሌሊትና ፡ ቀንም ፡ በመቅደሱ ፡ ያመልኩታል
በዙፋኑም ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው ፡ በእነርሱ ፡ ላይ ፡ ያድርባቸዋል
ከእንግዲህ ፡ ወዲስ ፡ አይራቡም ፡ ከእንግዲህም ፡ ወዲህ ፡ አይጠሙም
ፀሐይም ፡ ትኩሳትም ፡ ሁሉም ፡ ከቶ ፡ አይወርድባቸውም
በዙፋኑ ፡ መካከል ፡ ያለው ፡ በጉ ፡ እረኛቸው ፡ ይሆናልና
ወደ ፡ ሕይወትም ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ ይመራቸዋልና
እግዚአብሔርም ፡ እምባዎችን ፡ ሁሉ ፡ ከዓይናቸው ፡ ያብሳል [4]

ከታላቅ ፡ መከራ ፡ የመጡ ፡ ናቸው
በበጉ ፡ ደምም ፡ አነጹ ፡ ልብሳቸውን
በዙፋኑ ፡ ፊት ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ አሉ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ

አዝ፦ በረከትና ፡ ክብርም ፡ ጥበብም
ባለጸግነት ፡ ኃይልም ፡ ብርታትም
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ለተቀመጠው
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚመለሰው
ለታረደው ፡ በግ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው (፬x)

  1. የዮሐንስ ፡ ራዕይ ፭ ፡ ፱ - ፲ (Revelations 5:9-10)
  2. የዮሐንስ ፡ ራዕይ ፭ ፡ ፲፫ (Revelations 5:13)
  3. የዮሐንስ ፡ ራዕይ ፭ ፡ ፲፩ - ፲፪ (Revelations 5:11-12)
  4. የዮሐንስ ፡ ራዕይ ፯ ፡ ፲፫ - ፲፯ (Revelations 7:13-17)