ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ (Tentem Yaleh Zariem Yaleh) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(1)

የታረደው ፡ በግ
(Yetaredew Beg)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

የኃያላን ፡ ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ የሆንከው
ብርሃንን ፡ እንደልብስ ፡ የተላበስከው
ሁሉም ፡ በዙፋንህ ፡ ስር ፡ ይወድቁልሃል
ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብለው ፡ ይጠሩሃል

አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ
ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ

ሊውጠን ፡ ተነስቶ ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ
የጠላት ፡ ሠራዊት ፡ እልፍ ፡ ሆኖ ፡ ተነሳ
ሰልፉን ፡ ድል ፡ አድራጊ ፡ የአርያም ፡ እሳት
ፈጥኖ ፡ ደረሰልን ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ አባት

አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ
ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ

ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ ታሪክ ፡ ሲለዋወጥ
በዙፋኑ ፡ አርፎ ፡ ጸንቶ ፡ የሚቀመጥ
የተዘጋውን ፡ ማኅተም ፡ ብቻውን ፡ የፈታ
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ

አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ
ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ

ጠቢቡን ፡ ኃያሉን ፡ ማንንም ፡ ሳይፈራ
የጽድቅ ፡ ስራውን ፡ በዓለም ፡ የሚሰራ
ሃኪም ፡ ያልቻለውን ፡ በሽታ ፡ ሚፈውስ
ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ የዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ

አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ
ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ

ኢየሱስ ፡ በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ታወቀ
ዝናውም ፡ ገነነ ፡ ሄደ ፡ እየደመቀ
እናንተ ፡ አጋንንቶች ፡ ምን ፡ ሊውጣቹህ ፡ ነው
ሂዱ ፡ ተቃጠሉ ፡ ስፍራቹህ ፡ ጥልቁ ፡ ነው

አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ
ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በማደሪያህ ፡ ትኖራለህ
ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በመንግሥትህ ፡ ትኖራለህ