From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰው ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ ፡ ይከዳል
ጊዜን ፡ ጠብቆ ፡ ይርቃል
ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ የማይተው
ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ዕውቀትን ፡ አይቶ ፡ ይከዳል
አላፊ ፡ መሆኑን ፡ ዘንግቷል
እያየ ፡ የአሁን ፡ የአሁኑን
ረስቶ ፡ አወዳደቄን
አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)
ዘለዓለም (፪x)
ትካዜዬን ፡ ለእርሱ ፡ ጥዬ
የውስጤን ፡ መቃተት ፡ ጌታዬ
ሰው ፡ እንኳን ፡ ቢከዳ ፡ ቢጥል
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ይረዳል
ሃሳቤን ፡ የሚያውቅልኝ
ድካሜን ፡ የሚረዳልኝ
የውስጥ ፡ ጭንቀቴ ፡ የሚገባው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው?
አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)
ዘለዓለም (፪x)
አጽናኝ ፡ መስሎ ፡ ይጠጋል
ጓደኛ ፡ መስሎ ፡ ይቀርባል
ጠላትም ፡ በእርሱ ፡ ተጠቅሞ
ብርሃኔንም ፡ አጨልሞ
ግን ፡ የሚመካው ፡ የምጠጋው
የልቤን ፡ የማጫውተው
ድጋፍ ፡ መከታ ፡ የማደርገው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው?
አዝ፦ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)
ዘለዓለም (፪x)
|