አንቺ ፡ ቤተልሔም (Anchi Bethlehem) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(1)

የታረደው ፡ በግ
(Yetaredew Beg)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

ሕዝቡን ፡ ከኃጢአት ፡ ሚያድን ፡ ሚፈውስ
ድንቅ ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ ስሙም ፡ ኢየሱስ
የእስራኤል ፡ መሪ ፡ ታላቁ ፡ መስፍን
በቤተልሄም ፡ ተወለደልን (፪x)

አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ
አሜን

ሰባሰገል ፡ መጡ ፡ ከነበሩበት
ለተወለደው ፡ ህጻን ፡ ሊሰግዱለት
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ታላቁ ፡ ጌታ
ከላይ ፡ ወረደ ፡ ሕዝቡን ፡ ሊፈታ
ሊሆን ፡ ደስታ

አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ
አሜን

ዝማሬ ፡ በመላእክት ፡ አስተጋባ
እጣንና ፡ ከርቤም ፡ በበረት ፡ ገባ
በምድር ፡ ቅጥርም ፡ ውስጥ ፡ ጽድቅም ፡ ይሆናል
እግዚአብሔር ፡ ዓለሙን ፡ እንዲሁ ፡ ወዷል (፪x)

አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ
አሜን

ታናሽ ፡ ከተማ ፡ ቤተልሔም ፡ ሆይ
መድሃኒት ፡ ከአንቺ ፡ ወጥቶ ፡ የለም ፡ ወይ
ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ስግደት
ለህጻኑ ፡ ኢየሱስ ፡ እናቅርብለት (፪x)

አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ
አሜን

ኮኮብ ፡ ይወጣል ፡ በትር ፡ ይነሳል
ለእስራኤል ፡ መዳን ፡ ይሆንለታል
ተብሎ ፡ ተነግሮ ፡ ነበር ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ሆኗል
አምላክ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋራ ፡ ሊታረቅ ፡ ወዷል (፪x)

አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ
አሜን