አቤኔዘር (Abenezer) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(1)

የታረደው ፡ በግ
(Yetaredew Beg)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል
እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል
ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፪x)

አናልፈውም ፡ ብለን ፡ አለፍነውን ፡ የመከራው ፡ ዓይነት ፡ ብዙ ፡ ነው
መች ፡ ተሸንፈን ፡ እናውቃለን ፡ አሸናፊዎች ፡ እንበልጣለን
ይህ ፡ ያልፋል ፡ ብለን ፡ ያልገመትነው ፡ የእኛ ፡ ታሪካችን ፡ ብዙ ፡ ነው
እያለፍን ፡ በድል ፡ ጐዳና ፡ አሸበረቅን ፡ በምሥጋና

አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል
እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል
ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፪x)

በሃሩር ፡ ጊዜ ፡ ሆኖ ፡ ጥላ ፡ በፍላጻ ፡ ሁሉ ፡ ከለላ
ልጆቹን ፡ ፊት ፡ ፊት ፡ እየመራ ፡ ደርሰናል ፡ ጺዮን ፡ ተራራ
የድካሙ ፡ ጊዜ ፡ አብቅቶ ፡ በብርታት ፡ ሕይወት ፡ ተተክቶ
በሽብሸባ ፡ ፊቱ ፡ ዘለናል ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፡ ረድቶናል

አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል
እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል
ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር

አሁን ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያላችሁ ፡ አቤኔዘር ፡ የሆነላቹህ
በፊቱ ፡ ቅረቡ ፡ በዕልልታ ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
ከአመድ ፡ ከትቢያ ፡ ያነሳቹህ ፡ በዚህ ፡ ጉባኤ ፡ ስንቶች ፡ ናችሁ
ታዲያ ፡ ለምን ፡ ነው ፡ ዝምታ ፡ የታል ፡ ደስታችሁ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ

አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል
እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል
ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር

ይህ ፡ ያልፋል ፡ ብለን ፡ ያልገመትነው ፡ የእኛ ፡ ታሪካችን ፡ ብዙ ፡ ነው
እያለፍን ፡ በድል ፡ ጐዳና ፡ አሸበረቅን ፡ በምሥጋና
እንዲያ ፡ ሚከሰን ፡ ጠላታችን ፡ አሁን ፡ የታለ ፡ ከፊታችን
ኢየሱስ ፡ ስለነገሠ ፡ በጠንካራው ፡ ክንድ ፡ ተደቆሰ

አዝ፦ አቤኔዘር ፤ አቤኔዘር
እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ረድቶናል
እንደተለመደው ፡ ድንቅ ፡ አድርጐልናል
ባሕሩንም ፡ ከፍሎ ፡ አሻግሮናል ፡ አቤኔዘር (፫x)