የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጽ (Yewaytana Yemerara Leqso Demtse) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(2)

መፈታቴን ፡ አውጃለሁ
(Mefetatien Awejalehu)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

የምትወደው ፡ ልጅህን ፡ ወደ ፡ ተራራ ፡ ውሰደው
በእዚያም ፡ ለእኔ ፡ ክብር ፡ መስዋዕት ፡ አድርገህ ፡ ሰዋው
ጌታ ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል ፡ ብዬ ፡ ከቶ ፡ አልጠበኩም
ቢሆንም ፡ ሳስተያየው ፡ ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ አይበልጥም

እኔም ፡ ሳላወላውል ፡ ወደዚያ ፡ ስፍራ ፡ ደረስኩኝ
ልጄን ፡ ለመሰዋት ፡ መሰዊያውን ፡ ሰራሁኝ
እንጨትም ፡ ረበረብኩኝ ፡ ልጄን ፡ ይስሐቅ ፡ አሰርኩኝ
በዚያም ፡ አጋደምኩኝ ፡ እጄንም ፡ ዘረጋሁኝ

ድምጹ ፡ ከሰማይ ፡ መጣ ፡ ሲል ፡ እጅህን ፡ አትዘርጋ
አብርሃም ፡ እንደምትወደኝ ፡ በእውነት ፡ ዛሬ ፡ አየሁኝ
የእውነት ፡ በረከትን ፡ እባርክሃለሁኝ
ልጅህን ፡ ላልከለከልከኝ ፡ በራሴ ፡ ምላለሁኝ

አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን
መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ
ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ
ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ
በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ
ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ

ፈርዖን ፡ ሲያሳድደኝ ፡ ዳግም ፡ ባሪያው ፡ ሊያደርገኝ
በሰረገላው ፡ ብዛት ፡ በሰልፉ ፡ ሲነሳብኝ
ቀይ ፡ ባሕርም ፡ ከፊቴ ፡ ሞልቶ ፡ ተደቅኖብኝ
ማለፊያ ፡ መንገድ ፡ ጠፍቶኝ ፡ በፍርሃት ፡ ተሞላሁኝ

ጌታ ፡ ግን ፡ ቃሉን ፡ ሰጠኝ ፡ ብርሃኑን ፡ አበራልኝ
ባሕሩን ፡ እንድትከፍለው ፡ በትርህን ፡ አንሳ ፡ አለኝ
እኔም ፡ ለቃሉ ፡ ታዘዝኩ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ ተደገፍኩ
ባሕሩም ፡ ተከፈለ ፡ ጠላቴም ፡ ሰጥሞ ፡ ቀረ

አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን
መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ
ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ
ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ
በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ
ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ

ከብዙ ፡ የጠላት ፡ ሴራ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያተረፍኩህ
እንድታገለግለኝ ፡ ልቤን ፡ በአንተ ፡ ያሳረፍኩኝ
ብሎ ፡ እንደታማኝ ፡ ባሪያ ፡ ጌታ ፡ ስለቆጠረኝ
ወደ ፡ ነነዌ ፡ እንድሂድ ፡ መለዕክትን ፡ ሰጥቶ ፡ ላከኝ

እኔ ፡ ግን ፡ በምትኩ ፡ ተርሴስ ፡ ልሄድ ፡ ፈለኩ
ብዙ ፡ ዋጋ ፡ ከፈልኩ ፡ በመርከብ ፡ ተሳፈርኩ
እንዳልሰማ ፡ እየሆንኩኝ ፡ በፊትህ ፡ ኮበለልኩኝ
ቃሉን ፡ በመተላለፍ ፡ እግዚአብሔርን ፡ በደልኩኝ
እርሱ ፡ ግን ፡ መቼ ፡ ተወኝ ፡ አምርሮ ፡ ተከተለኝ
ነፋሳትን ፡ አዘዘ ፡ ማዕበሉን ፡ አስነሳብኝ
እንዲያውም ፡ ይባስ ፡ ብሎ ፡ ከባሕር ፡ ውስጥ ፡ ተጣልኩኝ
ሶስት ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ በዓሣ ፡ ሆድ ፡ አደርኩ

በመከራዬ ፡ ሳለሁ ፡ ወደእግዚአብሔር ፡ ጮህኩኝ
ይልቁንም ፡ በንስሃ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ተስማማሁ
ጌታዬም ፡ ይቅር ፡ አለኝ ፡ ዳግም ፡ ተጠቀመብኝ
ነነዌንና ፡ ጌታን ፡ ለማስታረቅ ፡ በቃሁኝ

አዝ፦ የዋይታና ፡ የመራራ ፡ ለቅሶ ፡ ድምጼን
መጽናናት ፡ ሲያቅተኝ ፡ በፊትህ ፡ ያለቀስኩትን
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሆኖ ፡ ተመለከተኝ
ድምጹንም ፡ አሰማኝ ፡ እንዲህ ፡ አለኝ
ዓይንህን ፡ ከእንባ ፡ ከልክል ፡ ድምጽህንም ፡ ከለቅሶ
በጣም ፡ ቶሎ ፡ ታያለህ ፡ እንባህ ፡ ከዓይንህ ፡ ታብሶ
ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ምርኮህም ፡ ተመልሶ