From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በላይ ፡ በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ በሰማይ ፡ የሚኖረው
ከጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ያወጣን ፡ ቀንበሩን ፡ የሰበረው
ዙፋኑ ፡ ከጥንት ፡ ብሩክ ፡ ነው ፡ ከልባችን ፡ ክብር ፡ እንስጠው
በሞቱ ፡ ሕይወት ፡ የሰጠን ፡ ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
አዝ፦ የታለ ፡ ዕልልታው ፡ ጭብጨባው ፡ ለኢየሱስ ፡ የሚገባው
ለከፈለው ፡ ዕዳችንን ፡ ለአዳናት ፡ ነፍሳችንን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምሥጋና ፡ እርሱ ፡ እምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ ለገለጠው ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
ምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን
ሕዝቡን ፡ ከስራት ፡ የፈታ ፡ ለክብሩ ፡ ያቆመን ፡ ጌታ
ድል ፡ በድል ፡ ያመላለሰን ፡ ጠላትን ፡ ያዋረደልን
በማዕዱ ፡ ዙሪያ ፡ ሰብስቦ ፡ እንደዚህ ፡ ላረሰረሰን
እረ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ ፡ ይህንን ፡ ላረገው ፡ ጌታ
አዝ፦ የታለ ፡ ዕልልታው ፡ ጭብጨባው ፡ ለኢየሱስ ፡ የሚገባው
ለከፈለው ፡ ዕዳችንን ፡ ለአዳናት ፡ ነፍሳችንን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምሥጋና ፡ እርሱ ፡ እምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ ለገለጠው ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
ምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን
ምህረቱ ፡ እጅግ ፡ ሰፊ ፡ ነው ፡ ይቅርታው ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ነው
ከነኃጢያታችን ፡ ወዶናል ፡ ልንከተለው ፡ ይገባናል
የነገርነውን ፡ ላልረሳ ፡ የለመንውን ፡ ላልረሳ
ለታላቁ ፡ አምላካችን ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ከልባችን
አዝ፦ የታለ ፡ ዕልልታው ፡ ጭብጨባው ፡ ለኢየሱስ ፡ የሚገባው
ለከፈለው ፡ ዕዳችንን ፡ ለአዳናት ፡ ነፍሳችንን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምሥጋና ፡ እርሱ ፡ እምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ ለገለጠው ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
ምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን
ሕዝቡን ፡ ከስራት ፡ የፈታ ፡ ለክብሩ ፡ ያቆመን ፡ ጌታ
ድል ፡ በድል ፡ ያመላለሰን ፡ ጠላትን ፡ ያዋረደልን
በማዕዱ ፡ ዙሪያ ፡ ሰብስቦ ፡ እንደዚህ ፡ ላረሰረሰን
እረ ፡ የታለ ፡ ዕልልታ ፡ ይህንን ፡ ላረገው ፡ ጌታ
አዝ፦ የታለ ፡ ዕልልታው ፡ ጭብጨባው ፡ ለኢየሱስ ፡ የሚገባው
ለከፈለው ፡ ዕዳችንን ፡ ለአዳናት ፡ ነፍሳችንን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምሥጋና ፡ እርሱ ፡ እምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ ለገለጠው ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
ምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ምሥጋና ፡ እርሱ ፡ እምላካችን ፡ ነውና
ጨለማውን ፡ ለገለጠው ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው
ምንጠብቀው ፡ ተስፋችን ፡ ይክበርልን ፡ አምላካችን ፡ አሜን (፪x)
|