ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምራለሁ (Selezih Hulgizie Zemeralehu) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(2)

መፈታቴን ፡ አውጃለሁ
(Mefetatien Awejalehu)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

ትላንትና ፡ ለሊቱን ፡ በሥጋዬ ፡ ጥሬያለሁ
አሁን ፡ ግን ፡ መረቦቼን ፡ በቃልህ ፡ እጥላለሁ
የበረከት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ ስታዘዘው ፡ ቃልህን
ተትረፈረፍኩኝ ፡ ዛሬ ፡ አይቻለሁ ፡ ሃይልህን (፫x)

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ

በዚህ ፡ ተራራ ፡ ታላቅ ፡ የሰባ ፡ ግብዣ ፡ እድርገህ
በብዙ ፡ ታምራቶች ፡ በደመና ፡ ተገልጠህ
ሌላውን ፡ አስክረሳ ፡ አስክመርጥ ፡ በዚህ ፡ መኖር
በብዙ ፡ ባርከኸኛል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ክበር (፫x)

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ

በትሬን ፡ ብቻ ፡ ይዤ ፡ ተሻገርኩ ፡ ዪርዳኖስን
የሁለት ፡ ክፍል ፡ ሰራዊት ፡ አርገኸኛል ፡ ዛሬ ፡ ግን
በጠላት ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ በዘይት ፡ ቀብተህ ፡ እራሴን
ላመላለስከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመስገን (፫x)

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ

በዚያ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ብቻዬን ፡ ሳለሁኝ
በድንገት ፡ ከአጠገቤ ፡ ምንጩ ፡ ፈለቀልኝ
አለቆች ፡ እየቆፈሩ ፡ በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ ላይ
የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ (፫x)

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ

በኤማኦስ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ሳለን
ኢየሱስ ፡ እራሱ ፡ ቀድሞ ፡ ይሄድ ፡ ነበር ፡ አብሮን
የልብን ፡ ሃዘን ፡ ነቅሎ ፡ ለሚሞላን ፡ በደስታ
ምሥጋና ፡ ያንስብናል ፡ ለአምላካችን ፡ ለጌታ (፫x)

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ

መስሎኝ ፡ ነበረ ፡ ለእኔስ ፡ በጠላቴ ፡ የተረታሁ
አቀበት ፡ ቁልቁለቱን ፡ ከቶ ፡ የማልወጣው
ከፍጥረት ፡ የታወቀው ፡ በድንቅ ፡ በታምራቱ
በብዙ ፡ ጥንቃቄው ፡ ጠብቆኛል ፡ በቤቱ
አኑሮኛል ፡ በቤቱ ፡ አክርሞኛል ፡ በቤቱ

አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ
በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ
በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ