መፈታቴን ፡ አውጃለሁ (Mefetatien Awejalehu) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(2)

መፈታቴን ፡ አውጃለሁ
(Mefetatien Awejalehu)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

ችግር ፡ መከራዬን ፡ ብሶቴንም ፡ ልውጣው
የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ አትራቅ
ለአንድ ፡ አፍታ ፡ ከልቤ ፡ ይሄንን ፡ ብነግረውን
ቀኜን ፡ ያሰረውን ፡ ገመዴን ፡ በጠሰው (፪x)

አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ
በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ
በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል
አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን

ኃይለኛና ፡ ታላቅ ፡ ነገር ፡ አደርጋለሁ
በእውነት ፡ የታመነ ፡ ቤትን ፡ እሰራለሁ
ታማኙ ፡ አምላኬ ፡ እንደተናገረው
በእርግጥ ፡ አድርጐታል ፡ ስሙን ፡ አከብራለሁ (፪x)

አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ
በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ
በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል
አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን

ናቡከደነጾር ፡ የተባለው ፡ ንጉሥ
ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ ከሰራዊት ፡ ቅዱስ
ባቢሎንን ፡ አይቶ ፡ በትዕቢት ፡ ታሰረ
ለሰባት ፡ ዘመናት ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ቀረ
ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሲያየው
ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ሕይወት ፡ ለክብር ፡ መለሰው
ይህንን ፡ ላደረገው ፡ ለታላቁ ፡ ጌታ
ምሥጋናን ፡ እንስጠው ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ (፪x)

አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ
በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ
በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል
አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን

እስራትን ፡ ፈቶ ፡ ቀንበር ፡ የሰበረ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ በጣም ፡ የከበረ
ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ሚታዘዙለት
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት (፪x)

አዝ፦ መፈታቴን ፡ አውጃለሁ ፡ ለጠላቴም ፡ እነግረዋለሁ
በበጉ ፡ ፊት ፡ እሆናለሁ ፡ የድል ፡ ዜማን ፡ አዜማለሁ
በሕዝቡ ፡ ፊት ፡ አክብሮኛል ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀብቶኛል
አከብረው ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ አሜን (፪x)