ፍሬ ፡ አፍርተህ (Ferie Afreteh) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(2)

መፈታቴን ፡ አውጃለሁ
(Mefetatien Awejalehu)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

ብዙ ፡ አመታት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ስትወጣ ፡ ስትወርድ
ስለ ፡ ስሜ ፡ ስትሰደብ ፡ ስትመታ ፡ ስትዋረድ
ልመጣ ፡ ስል ፡ ትንሽ ፡ ሲቀር ፡ ልጐበኝህ
ልፋትህን ፡ ከንቱ ፡ አድርገህ ፡ ምነው ፡ ሸሸህ

አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ
ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ
የድካምኽን ፡ የልፋትህን
እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን

እንደጀመርክ ፡ ብትጨርስ ፡ ያን ፡ ፍቅርህን
ነፍሳት ፡ ለማዳን ፡ የነበረህን ፡ ጥማትህን
ስትዘምር ፡ ስትጨልይ ፡ ጊዜህን ፡ ሰጥተህ
ልሸልምህ ፡ ልመጣ ፡ ስል ፡ ምነው ፡ ሸሸህ

አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ
ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ
የድካምኽን ፡ የልፋትህን
እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን

የጸለይከውን ፡ ጸሎትህን ፡ ልመናህን
ላብሰው ፡ ስል ፡ ያነባኸውን ፡ እንባህን
በአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ልጄ ፡ ብዬ ፡ ስጠራህ
ከቦታ ፡ አጣሁ ፡ እጄን ፡ ስዘረጋልህ

አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ
ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ
የድካምኽን ፡ የልፋትህን
እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን

ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ የዘለልከው ፡ የወጣኸው
እንደ ፡ ቃዬል ፡ ፍቅሬን ፡ ኃይሌን ፡ የቀመስከው
እኔ ፡ ነበርኩኝ ፡ ውበትና ፡ ደም ፡ ግባትህ
ልመጣ ፡ ስል ፡ ይሄን ፡ ረስተህ ፡ ምነው ፡ ሸሸህ

አዝ፦ ፍሬ ፡ አፍርተህ ፡ እንዳገኝህ
ስትተጋ ፡ ስጐበኝህ
የድካምኽን ፡ የልፋትህን
እንደከፍልህ ፡ ዋጋህን