እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ (Egziabhieren Tebeqie) - ታደሰ ፡ እሸቴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታደሰ ፡ እሸቴ
(Tadesse Eshete)

Lyrics.jpg


(2)

መፈታቴን ፡ አውጃለሁ
(Mefetatien Awejalehu)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታደሰ ፡ እሸቴ ፡ አልበሞች
(Albums by Tadesse Eshete)

ነገ ፡ በሕይወትህ ፡ ድንቅ ፡ አደርጋለሁ
ብቻ ፡ አንተ ፡ ተቀደስ ፡ እኔ ፡ ሰራለሁ
ብሎ ፡ ጌታ ፡ አሰበኝ ፡ ቃሉን ፡ አክብሮ
ምርኮዬን ፡ መልሷል ፡ ስሜን ፡ ቀይሮ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል

ጌታውን ፡ ተማምኖ ፡ የሚጠባበቅ
ኃይሉ ፡ ታደሰ ፡ እንጂ ፡ ዘላለም ፡ አይወድቅ
እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያረኩት
ጸሎቴን ፡ መልሷል ፡ ኑ ፡ ስሙን ፡ ባርኩት

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል

በለስን ፡ ጠብቆ ፡ ፍሬን ፡ የበላ
ከጌታው ፡ ጋር ፡ ሆኖ ፡ ያልቀረ ፡ ኋላ
አከናውኖልኛል ፡ ምኔን ፡ ልክፈለው
የሚል ፡ በዕልልታ ፡ ጌታን ፡ ያክብረው

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል

ሥጋዬን ፡ በጥርሴ ፡ እነክሳለሁኝ
ቢገድለኝም ፡ እርሱን ፡ እጠብቃለሁኝ
ብሎ ፡ ለጠበቀው ፡ ጌታን ፡ በእምነት
ሁለት ፡ እጥፍ ፡ መጣ ፡ የኢዮብ ፡ በረከት

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል

እረድኤቴና ፡ መድሃኒቴ
አከናውኖልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ
በፊቱ ፡ ዘላለሁ ፡ እንደ ፡ እንቦሳ
ስላራቀው ፡ ከእኔ ፡ ያንን ፡ አበሳ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል

ልጄ ፡ ልብህን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ና
እሰራለሁ ፡ ብሎ ፡ አባበለና
እኔም ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር ፡ ወዲያው ፡ ስታረቅ
ጸሎቴን ፡ መለሰው ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም
ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም
በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል
ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል (፪x)