From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ አለፈ ፡ ከተናገርካቸው
አብርሃምና ፡ ሳራን ፡ ተስፋ ፡ ፈተናቸው
ከዚህ ፡ የተነሳ ፡ እርምጃን ፡ ወሰዱ
አንተንም ፡ ቀደሙ ፡ እስማኤልን ፡ ወለዱ
ግን ፡ አንተ ፡ ጌታችን ፡ ስለተስፋህ ፡ ብለህ
ይስሐቅን ፡ አምጥተህ ፡ ቃልህን ፡ ፈጸምህ (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም
ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም
ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ
በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ
ክብርህን ፡ ትገልጻልህ
ወንድሞቹ ፡ ሲሰግዱ ፡ ዮሴፍ ፡ ህልምን ፡ አየ
ግን ፡ የኖረው ፡ ኑሮ ፡ ከዚህ ፡ የተለየ
ቃልህ ፡ እስኪመጣለት ፡ እርሱም ፡ ተፈተነ
በእርኩሰት ፡ በኃጢአት ፡ ላይ ፡ ሁሌ ፡ እየጨከነ
የሚጐበኝበት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ መጣ
ከእዛ ፡ ጉስቁልናው ፡ ከመከራ ፡ ወጣ (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም
ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም
ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ
በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ
ክብርህን ፡ ትገልጻልህ
ሃና ፡ መካኗ ፡ ሴት ፡ ብዙ ፡ አለቀሰች
በወገኖች ፡ ሳይቀር ፡ እየተነቀፈች
እርሷም ፡ እንደ ፡ ሰዎች ፡ ዘመኗ ፡ ደረሰ
ልቧ ፡ በአንተ ፡ ጸና ፡ ታሪኳም ፡ ታደሰ
አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ስራው ፡ ያስደንቃል
የምስኪኑን ፡ እንባ ፡ በጊዜው ፡ ያደርቃል (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም
ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም
ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ
በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ
ክብርህን ፡ ትገልጻልህ
በጣም ፡ የምትወደው ፡ አልዓዛር ፡ ታሟል
የሚል ፡ ድምጽ ፡ ከሰማ ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ሆኖታል
የሞተውን ፡ ሊያስነሳ ፡ እንባቸውን ፡ ሊያብስ
በራሱ ፡ ጊዜ ፡ መጣ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ
ዛሬም ፡ ብንጠብቀው ፡ በመጠበቂያችን
እግዚአብሔር ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ሊገልጽልን (፪x)
አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም
ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም
ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ
በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ
ክብርህን ፡ ትገልጻልህ
|