የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ (Yeziema Gizie Derese) - ሱራፌል ፡ ደምሴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ሱራፌል ፡ ደምሴ
(Suraphel Demissie)

Suraphel Demissie 1.jpg


(1)

የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ
(Yeziema Gizie Derese)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:55
ጸሐፊ (Writer): ልእልት ፊልጶስ
(Lielt philipose
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሱራፌል ፡ ደምሴ ፡ አልበሞች
(Albums by Suraphel Demissie)

የዜማ ጊዜ ደረሰ
ያለቀሰ እንባው ታበሰ
እየሱስ መጣ ወደርሱ
ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ
 
ዘሬን ፡ ተሸክሜ ፡ እያለቀስኩ ፡ ሄድኩኝ
ዛሬ ፡ ነዶ ፡ ይዤ ፡ ለክብሩ ፡ ዘመርኩኝ
ለቅሶ ማታ ነበር ጠዋት ደስታ ሆኗል
የአምላኬ ክብር በኔ ላይ ጨምሯል
   
  እራሴን ሰጥቼ ላምልከው ፈቅጄ
    ለኔ ፈጥኖ ደራሽ እየሱስ ወዳጄ

  እራሴን ፡ ሰጥቼ ፡ ላምልከው ፡ ፈቅጄ
  እንባየ ታብሷል
  በርሱ በወዳጄ

የዜማ ጊዜ ደረሰ
ያለቀሰ እንባው ታበሰ
እየሱስ መጣ ወደርሱ
ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ 2×
  
ዛሬማ ግዜው ነውና
  ዛሬማ ላሰማ ዜማ
  ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ
  ዛሬማ ላሰማ እልልታ
  ዛሬማ ግዜው ነውና
  ዛሬማ ላሰማ ዜማ
  ዛሬማ ክረምት አለፈ
  ዛሬማ ሀዘን ጨለማ

ምድረበዳውና ደረቁ ምድር
ደስም ይላቸዋል ሀሴት ያደርጋል
ብሎ ያለው ቃሉ ዛሬ ተፈጽሟል
ዲዳው ተፈውሶ ለክብሩ ያዜማል
  
 እራሴን ሰጥቼ
  ላምልከው ፈቅጄ
  ለኔ ፈጥኖ ደራሽ
  እየሱስ ወዳጄ
 እራሴን ሰጥቼ
 ላምልከው ፈቅጄ
 እንባየ ታብሷል
 በርሱ በወዳጄ
ዛሬማ ግዜው ነውና
ዛሬማ ላሰማ ዜማ
ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ
ዛሬማ ላሰማ እልልታ
ዛሬማ ግዜው ነውና
ዛሬማ ላሰማ ዜማ
ዛሬማ ክረምት አለፈ
ዛሬማ ሀዘን ጨለማ

ክረምቱ አለፈ አዲስ ዘመን መጣ
ወይኖቹም አበቡ ፡ በለሱም ጎመራ
ከአለት ንቃቃት ወጣሁ ልዘምር
ማዳኑን ላወራ ድንቁን ልናገር
    የዜማ ግዜ ደረሰ
    ያለቀሰ እንባው ታበሰ
    እየሱስ መጣ ወደርሱ
    ጠላቶቹ/ከሳሾቹ ማቅ ለበሱ
ዛሬማ ግዜው ነውና
ዛሬማ ላሰማ ዜማ
ዛሬማ ለረዳኝ ጌታ
ዛሬማ ላሰማ እልልታ
ዛሬማ ግዜው ነውና
ዛሬማ ላሰማ ዜማ
ዛሬማ ክረምት አለፈ
ዛሬማ ሀዘን ጨለማ