ተመስገን (Temesgen) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ:- ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታችን ፡ ተመስገን
በእውነት ፡ ተመስገን ፡ ከልባችን ፡ ተመስገን (፪x)

ሕዝቡን ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ የመራ
ቀን ፡ በደመና ፡ አምድ ፡ ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ
ዛሬም ፡ በዚህ ፡ አለ ፡ ሊመራ ፡ ሊያሳድግ
እባክህ ፡ አትሂድ ፡ በራስህ ፡ መንገድ (፫x)

አዝ:- ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታችን ፡ ተመስገን
በእውነት ፡ ተመስገን ፡ ከልባችን ፡ ተመስገን (፪x)

ዳንኤል ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ መስኮት ፡ በሩን ፡ ከፍቶ
ይጸልይ ፡ ጀመረ ፡ ለአምላክ ፡ ተንበርክኮ
ጠላትም ፡ ሊያጠፋው ፡ ምክርን ፡ ሁሉ ፡ መክሮ
በጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ጣለው ፡ በቃ ፡ አለቀ ፡ ብሎ

ከእሱ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል
በአንበሳ ፡ መካከል ፡ እንቅልፍን ፡ ይሰጣል
አንተን ፡ የሚያስፈራህ ፡ ዛሬ ፡ የትኛው ፡ ነው
እባክህ ፡ በርሱ ፡ ታመን ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው (፫x)

ከዘመን ፡ ዘመን ፡ አሸጋግሮ ፡ አመታቶችን ፡ አሳልፎ
ቀኖቹን ፡ በመልካም ፡ ለውጦ
እዚህ ፡ ደረስኩኝ ፡ በጌታ ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ
እዚህ ፡ ደረስኩኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ (፪x)

ጠላት ፡ ያሰበው ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ አልሆነም ፡ እቅዱም ፡ ከቶ ፡ አልተከናወነም
እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱ ፡ እንደ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለመልካም
እንደሚደረግ ፡ እኔ ፡ አወቅኩ ፡ እንደሚደረግ ፡ ተረዳሁ (፪x)

እስኪ ፡ ያለፈ ፡ ሰው ፡ የታል ፡ የተሸጋረ
አሮጌው ፡ ልብሱ ፡ በአዲስ ፡ የተቀየረ
ጭጋግ ፡ ጨለማው ፡ እንደጉም ፡ የተበተነ
ሆ ፡ ይበል ፡ በምስጋና ፡ ይግባ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
ለጌቶች ፡ ጌታ ፡ ይዘምር ፡ ያምጣ/ያግባ ፡ ስለቱን
(፪x)

ዝም ፡ ብዬ ፡ እዘምራለሁ
ለኔ ፡ የሚያስብ ፡ ጌታ ፡ አግኝቻለሁ
(፪x)
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ ሹመት ፡ ከፍታን ፡ ከፊቴ ፡ እያየሁ
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ በተራራ ፡ ላይ ፡ እቀመጣለሁ
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ ትልቅነቱን ፡ እናገራለሁ

አንድ ፡ ጌታ ፡ አንድ ፡ አምላክ ፡ አንድ ፡ ወዳጅ ፡ አለ
ለዓለም ፡ ቤዛ ፡ መድህን ፡ መልስም ፡ የሆነ (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የለወጠው
ታሪኬን ፡ ከስር ፡ የገለበጠው (፪x)

በአዲሱ ፡ አቅማዳ ፡ አዲስ ፡ የወይን ፡ ጠጅ
ሞልቶ ፡ ይፈሳል ፡ ከኔ ፡ ወደ ፡ ደጅ
ያረካል ፡ እርሱ ፡ እኔ ፡ ረክቻለሁ
ግቡና ፡ ጠጡ ፡ ጋብዣችኋለሁ (፪x)


ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ኢየሱስ ፡ መልስ ፡ ነው (፪x)
ወግ ፡ ማዕረግ ፡ በርሱ ፡ ነው (፯x)

ከዘመን ፡ ዘመን ፡ አሸጋግሮ ፡ አመታቶችን ፡ አሳልፎ
ቀኖቹን ፡ በመልካም ፡ ለውጦ
እዚህ ፡ ደረስኩኝ ፡ በጌታ ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ
እዚህ ፡ ደረስኩኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ

ጠላት ፡ ያሰበው ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ አልሆነም ፡ እቅዱም ፡ ከቶ ፡ አልተከናወነም
እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱ ፡ እንደ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለመልካም
እንደሚደረግ ፡ እኔ ፡ አወቅኩ ፡ እንደሚደረግ ፡ ተረዳሁ (፪x)

እስኪ ፡ ያለፈ ፡ ሰው ፡ የታል ፡ የተሸጋረ
አሮጌው ፡ ልብሱ ፡ በአዲስ ፡ የተቀየረ
ጭጋግ ፡ ጨለማው ፡ እንደጉም ፡ የተበተነ
ሆ ፡ ይበል ፡ በምስጋና ፡ ይግባ ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
ለጌቶች ፡ ጌታ ፡ ይዘምር ፡ ያግባስለቱን
(፪x)

ዝም ፡ ብዬ ፡ እዘምራለሁ
ለኔ ፡ የሚያስብ ፡ ጌታ ፡ አግኝቻለሁ
(፪x)
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ ሹመት ፡ ከፍታን ፡ ከፊቴ ፡ እያየሁ
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ በተራራ ፡ ላይ ፡ እቀመጣለሁ
ነገንም ፡ በርሱ ፡ እረማመዳለሁ ፡ ትልቅነቱን ፡ እናገራለሁ

አንድ ፡ ጌታ ፡ አንድ ፡ አምላክ ፡ አንድ ፡ ወዳጅ ፡ አለ
ለዓለም ፡ ቤዛ ፡ መድህን ፡ መልስም ፡ የሆነ (፪x)

እርሱ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የለወጠው
ታሪኬን ፡ ከስር ፡ የገለበጠው (፪x)

በአዲሱ ፡ አቅማዳ ፡ አዲስ ፡ የወይን ፡ ጠጅ
ሞልቶ ፡ ይፈሳል ፡ ከኔ ፡ ወደ ፡ ደጅ
ያረካል ፡ እርሱ ፡ እኔ ፡ ረክቻለሁ
ግቡና ፡ ጠጡ ፡ ጋብዣችኋለሁ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ኢየሱስ ፡ መልስ ፡ ነው (፪x)
ወግ ፡ ማዕረግ ፡ በርሱ ፡ ነው (፯x)