ጠቢባኖች (Tebibanoch) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ ጠቢባኖች ፡ አዋቂዎች ፡ ተምረናል ፡ ያሉ
ኃይልህን ፡ ለማወቅ ፡ ግን ፡ ከቶውን ፡ አልቻሉም
ለደካማው ፡ ለታናሹ ፡ ጥበብን ፡ ሞላኸው
በኖረበት ፡ ምድር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ አለበስከው

መች ፡ በራሴ ፡ በጉልበት ፡ እኔ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
አውቀዋለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ (፪x)

አሁንማ ፡ በዛ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ
ተቆጥሮ ፡ አይዘለቅ ፡ የጌታ ፡ ምህረቱ ፡ የእርሱ ፡ ቸርነቱ (፪x)

ከእግዚአብሔር ፡ በቀር ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ሲወጣ ፡ ሲገባ ፡ በማን ፡ ይታመናል
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አይሆንልኝ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ከቶ ፡ አልውልም ፡ አላድርም ፡ ስሙን ፡ ሳልጠራ

ቅር ፡ ቅር ፡ ቅር ፡ ይለኛል
አባቴ ፡ አይደለ ፡ እርሱ ፡ ይርበኛል ፡ ይናፍቀኛል
ድምጹ ፡ ምግቤ ፡ ነው ፡ ያበረታታኛል
ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ ሞገስ ፡ ሆኖኛል
ስሙን ፡ ስጠራ ፡ እጅግ ፡ ያኮራኛል
ማይነቃነቅ ፡ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆኖኛል

እውነት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ፍቅር ፡ ነው ፡ የምትሉ
ጌታ ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ከኔ ፡ ጋር ፡ እልል ፡ በሉ
እውነት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ የምትሉ
አባት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ከኔ ፡ ጋር ፡ እልል ፡ በሉ

አዝ፦ ጠቢባኖች ፡ አዋቂዎች ፡ ተምረናል ፡ ያሉ
ኃይልህን ፡ ለማወቅ ፡ ግን ፡ ከቶውን ፡ አልቻሉም
ለደካማው ፡ ለታናሹ ፡ ጥበብን ፡ ሞላኸው
በኖረበት ፡ ምድር ፡ ሞገስ ፡ ሞገስ ፡ አለበስከው

መች ፡ በራሴ ፡ በጉልበት ፡ እኔ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
አውቀዋለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ (፪x)

አሁንማ ፡ በዛ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ
ተቆጥሮ ፡ አይዘለቅ ፡ የጌታ ፡ ምህረቱ ፡ የእርሱ ፡ ቸርነቱ (፪x)

ከእግዚአብሔር ፡ በቀር ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ሲወጣ ፡ ሲገባ ፡ በማን ፡ ይታመናል
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አይሆንልኝ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ከቶ ፡ አልውልም ፡ አላድርም ፡ ስሙን ፡ ሳልጠራ

ቅር ፡ ቅር ፡ ቅር ፡ ይለኛል
አባቴ ፡ አይደለ ፡ እርሱ ፡ ይርበኛል ፡ ይናፍቀኛል
ድምጹ ፡ ምግቤ ፡ ነው ፡ ያበረታታኛል
ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ ሞገስ ፡ ሆኖኛል
ስሙን ፡ ስጠራ ፡ እጅግ ፡ ያኮራኛል
ማይነቃነቅ ፡ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆኖኛል

እውነት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ፍቅር ፡ ነው ፡ የምትሉ
ጌታ ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ከኔ ፡ ጋር ፡ እልል ፡ በሉ
እውነት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ የምትሉ
አባት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ከኔ ፡ ጋር ፡ እልል ፡ በሉ

አምናም ፡ ስገረም ፡ ስደነቅ ፣ ዘንድሮ ፡ መጣ ፡ በእጥፍ
ከርሱ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ ተስማምቶኛል ፣ እንደ ፡ መህልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ይዞኛል
ወዲህ ፡ ወዲያ ፡ አልል ፡ ተመችቶኛል (፪x)

ምቹ ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ አባት ፡ ነው ፡ የምትሉ
እንደ ፡ እናት ፡ ነው ፡ የምትሉ ፣ ከኔ ፡ ጋር ፡ እልል ፡ በሉ (፪x)