ስላንተ ፡ ቢወራ (Selante Biwera) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር
የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን
ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረከውን ፡ ነገር
(፪x)

ሞቴ ፡ በሕይወት ፡ ተቀይሮልኛል ፡ ኑር ፡ ብለህ ፡ ፈቅደህልኛል
በምድር ፡ በርዝመቷ ፡ በስፋቷ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በከፍታ
እንድወጣ ፡ እንድገባ ፡ ፈቅደህልኛል
የሚይዘኝ ፡ የለም ፡ ከፊቴ ፡ ወጥተህልኛል (፪x)

አዝ ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር
የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን
ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረግከውን ፡ ነገር
(፪x)

አርነት ፡ ነፃ ፡ ወጥቻለሁ ፡ እርሱ ፡ ለቅቆኝ ፡ ተለቅቄያለሁ
አልሄድ ፡ ወደኋላ ፡ ወደፊት ፡ እራመዳለሁ
እርሱ ፡ ከከፈተው ፡ አትገባም ፡ የሚለኝ ፡ ማነው

ሸክሜን ፡ ጣለ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረ ፣ እዳዬም ፡ በርሱ ፡ ተከፈለ
አለኝ ፡ አልጥልህም ፡ አልተውህም ፣ ፍጹም ፡ ከእጄ ፡ አላወጣህም
መርጬሃለሁ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ አያስፈራህም

አዝ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር
የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን
ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረከውን ፡ ነገር
(፪x)

እየገባኝ ፡ መጣ ፡ አሁን ፡ እየተረዳሁ ፣ ነገሬ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ሰምሮ ፡ እያየሁ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ለካ ፡ ከላይ ፡ ታዞ ፡ ነው
አርፌ ፡ እንድኖር ፡ ቀድሞ ፡ ስራዬን ፡ ሰርቶት ፡ ነው
ከተመስገን ፡ ሌላ ፡ ታዲያ ፡ የምለው ፡ ምንድነው

ተመስገን (፬x)
የኔ ፡ ጌታ ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር (፬x)