From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው
ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው
አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ (፪x) (ሃሌሉያ)
ባህሩን ፡ በተዓምር ፡ የከፈለ
አንካሳውን ፡ ደግሞ ፡ ያዘለለ
እውሩን ፡ በእጆቹ ፡ ዳሰሰና
በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለው ፡ ፈወሰና (፪x)
ጴጥሮስን ፡ በውሃ ፡ ላይ ፡ ያራመደ
ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ ጸጥ ፡ ያረገ
እንደሱ ፡ የሚሆን ፡ የትም ፡ የለም
ይባረክ ፡ ይመስገን ፡ ለዘላለም (፪x)
አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው
ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው
አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) (ሃሌሉያ)
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ምድረ ፡ በዳ
ሕዝቡን ፡ የሚመግብ ፡ የሚረዳ
በጠሩትም ፡ ጊዜ ፡ ከተፍ ፡ የሚል
የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያስተማምን
በጠሩትም ፡ ጊዜ ፡ ከተፍ ፡ የሚል
የሚያኮራ ፡ ጌታ ፡ የሚያስተማምን (፪x)
ዛሬም ፡ ለኔ (ዛሬም ፡ ለኔ) ፡ በዘመኔ (በዘመኔ)
ድንቅ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ (፪x)
አዝ፦ ያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው
ያው ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ያው ፡ ነው
ጥንትም ፡ የሚሰራ ፡ አሁንም ፡ ያው ፡ ነው
አልተለወጠም ፡ ኃይሉ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) (ሃሌሉያ)
እግዚአብሔርም ፡ እንዲህ ፡ ይላል
ጥራኝ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ እሰማሃለሁ
የማታውቀውን ፡ ታላቅና ፡ ኃይለኛ ፡ ነገር ፡ አሳይሃለሁ
በቃሌ ፡ እኔ ፡ እተጋለሁ ፡ ድምጽህን ፡ ፈጥኜ ፡ እሰማለሁ
ከቃሌ ፡ ጋራ ፡ እሆናለሁ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ እመን ፡ እሰራለሁ (፪x)
ዛሬም ፡ ለኔ (ዛሬም ፡ ለኔ) ፡ በዘመኔ (በዘመኔ)
ድንቅ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱሱ ፡ ጌታዬ ፡ (፪x)
|