እግዚአብሔር ፡ አንተ (Egziabhier Ante) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ
አምባዬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ ኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ
ኢየሱሴን ፡ ኢየሱሴን ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ (፪x)

እርሱ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስደነግጥም ፡ አድኖኛል
እውነት ፡ እንደጋሻ ፡ ሆኖ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኛል
መድኃኒት ፡ መድኃኒት ፡ እርሱ ፡ ሆኖልኛል (፪x)

በቀንም ፡ ከሚበር ፡ ከሌሊትም ፡ ግርማ ፡ አድኖኛል
በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ስለኔ ፡ መላእክቱ ፡ ታዘዋል
ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ እንዴት ፡ ያስተማምናል (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ
አምባዬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ ኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ
ኢየሱሴን ፡ ኢየሱሴን ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ (፪x)

በተኩላና ፡ በእባብ ፡ ላይም ፡ እጫማለሁ
አንበሳ ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጣለሁ
በርሱ ፡ ተማምኜ ፡ ሁሉንም ፡ አልፋለሁ
ስሙንም ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እጠራለሁ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x)
ኢየሱስ ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ ፡ ኢየሱስ

ሃሌሉያ ፡ (፬x)