From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እውነቱ ፡ አዳነኝ ፡ እውነት ፡ ነው
ፈልጐ ፡ አገኘኝ ፡ ፍቅር ፡ ነው
አደራረጉ ፡ ልዩ ፡ ነው
ከምንገምተው ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ ልናገር ፡ ተደርጐልኛል
ቀንበሬም ፡ በርሱ ፡ ተሰብሮልኛል
አርነት ፡ ወጣሁ ፡ ነፃ ፡ አውጥቶኛል
ከዚያች ፡ ሩጫ ፡ እኔን ፡ ፈቶኛል
የተፈታ ፡ ሰው ፡ የተለቀቀ
መውጣት ፡ መግባቱ ፡ የተጠበቀ
ያመሰግናል ፡ ያመሰግናል ፡ ጊዜው ፡ ሁኔታ ፡ መች ፡ ያስቆመዋል
ያመሰግናል ፡ ያመሰግናል ፡ ማግኘት ፡ ማጣቱ ፡ መች ፡ ያስቆመዋል
ያኔ ፡ በልጅነት ፡ ገና ፡ መጀመሪያ
ጌታ ፡ ተናገረኝ ፡ በኔ ፡ እንደሚሰራ
የተናገረው ፡ ቃል ፡ ጊዜውን ፡ ጠብቆ
ሲፈጸም ፡ በዓይኔ ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ አይረሳም ፡ እኮ (፪x)
አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት
እንደማይረሳ ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት
አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት
እንደማይጥል ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት
አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት
ረዳት ፡ መሆኑን ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት
አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት
ትልቅነቱን ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት
ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ረዳት ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ አባት
ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ፈዋሽ ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ፍቅር
ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ልዩ ፡ ነው ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ልዩ ነው
እርሱ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነው
እርሱ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነው
እርሱ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው
እርሱ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x)
|