በመጀመሪያ (Bemejemeria) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
በመጀመሪያ ፡ በመጀመሪያ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

አዝበመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x)

ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ይመጣል
የልቤ ፡ መሻት ፡ ይሆናል
እንደተጻፈው ፡ አደርጋለሁ
በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

ሰው ፡ ባለው ፡ በሃብቱ ፡ ምን ፡ ቢኮራ
ቢማር ፡ ሊቅ ፡ ቢሆን ፡ ታሪክ ፡ ቢሰራ
ጌታ ፡ ከሌለው ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ነው
በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)

አዝበመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x)

ዳዊትም ፡ ኖረ ፡ እድሜ ፡ ዘመኑን
መጀመሪያ ፡ አርጐ ፡ እግዚአብሔርን
የሚቋቋመው ፡ አልነበረም
መንግስቱ ፡ ጸና ፡ ለመለመ

የእግዚአብሔር ፡ ልቡ ፡ እንዳረፈበት
እንደልቤ ፡ እንዳለው ፡ እንደኮራበት
እንደእምነት ፡ አባቴ ፡ እንደዳዊት
አስደስታለሁ ፡ የጌታን ፡ ልብ

አዝበመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x)
ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፬x)