አባቴ ፡ ኢየሱስ (Abatie Eyesus) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 1.png


(1)

ይገርማል
(Yegermal)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ
አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት
ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x)

የደረሰበት ፡ ያውቃል ፡ ተስፋው ፡ የጨለመበት
በቃ ፡ አለቀ ፡ ብሎ ፡ ሞቱን ፡ ሲጠባበቅ
ድል ፡ በድል ፡ አድራጊው ፡ ጌታዬ ፡ ደርሶለት
ሳቅ ፡ በሳቅ ፡ ያረገው ፡ ከላዩ ፡ ገፎለት (፬x)

አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ
አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት
ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x)

በምድረ ፡ በዳ ፡ ውስጥ ፡ አጋር ፡ እንዲያ ፡ ተጨንቃ
ሲሞት ፡ እንዳታየው ፡ ልጇን ፡ አርቃ ፡ ጥላ
ድምጿን ፡ አሰምታ ፡ በጣም ፡ አለቀሰች
ማነው ፡ ሚደርስልኝ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ አለች
እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ድምጻቸውን ፡ ሰማ
የጨለመውን ፡ ሕይወት ፡ እንደገና ፡ አበራ (፬x)

አዝ፦ አቤት ፡ እርሱ ፡ ሲያውቅበት ፡ ኢየሱሴ
አቤት ፡ ሲችልበት ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ማውጣት
ከጭንቀት ፡ ማሳረፍ (፪x)

የሞት ፡ ፍርሃት ፡ መጥቶ ፡ ዙሪያዬንም ፡ ከቦኝ
መሄጃ ፡ ማምለጫ ፡ ሁሉም ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ
ተጨንቄ ፡ ሳለሁ ፡ ጌታ ፡ ደርሶልኛል
ሸክሜን ፡ አራግፎልኝ ፡ በደስታ ፡ ሞልቶኛል (፬x)

እንደሰው ፡ አይደለም (፰x)

ይገርመኛል ፡ እዚህ ፡ መድረሴ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ሰው ፡ መሆኔ
ይገርመኛል ፡ እኔ ፡ ማለፌ