የእግዚአብሔር ፡ ጊዜ (Yegziabhier Gizie) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
የእግዚአብሔር ፡ ጊዜ ፡ የተወደደ
ደረሰ ፡ ለእኔ ፡ እርሱ ፡ የፈቀደው
የማጨድ ፡ ጊዜ ፡ የመከር ፡ ዘመን
መጥቷል ፡ ከፊቴ ፡ የመከናወን (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል
አትችልም ፡ አይሆንም ፡ የሚለው ፡ የታል (፪x)

ዘመን ፡ መጣ ፡ ለእኔ (፰x)
ያላየሁትን ፡ ባይኔ ፡ የማይበት ፡ ያልሰማሁትን ፡ የምሰማበት
በህልውናው ፡ ምጥለቀለቅበት ፡ ክብሩን ፡ እያየሁ ፡ የማመልክበት
(፪x)

ይሆናል ፡ ያለው ፡ ይሆናል
አትችልም ፡ አይሆንም ፡ የሚለው ፡ የታል (፪x)

ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ ሊያሳይ ፡ መንፈሱ ፡ መጣ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)

ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ ሊያሳይ ፡ አባቴ ፡ መጣ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)

እኔ ፡ የሚገርመኝ ፡ እኔ ፡ የሚደንቀኝ
ይህ ፡ ግዙፍ ፡ ሰማይ ፡ ይህ ፡ ግዙፍ ፡ ምድር
ሌላ ፡ አልተናገርክ ፡ ሌላ ፡ አላልካቸው
በአንድ ፡ ቃል ፡ ብቻ ፡ አጸናሃቸው (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል
አትችልም ፡ አይሆንም ፡ የሚለው ፡ የታል (፪x)

ሌሊቱን ፡ ሙሉ ፡ ቢጥር ፡ ቢደክም
መረቡ ፡ ባዶ ፡ ዓሣ ፡ የለውም
ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ካልተናገረው
ፈቀቅ ፡ በልና ፡ ወደጥልቁ ፡ ጣለው (፪x)

እንዳለው ፡ መረቡ ፡ ሞላ
ተዐምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ የሰራው ፡ ስራ (፪x)

ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ ሊያሳይ ፡ መንፈሱ ፡ መጣ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)

ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)
ምህረቱን ፡ ለእኔ ፡ ሊያሳይ ፡ አባቴ ፡ መጣ ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፪x)