የድል ፡ ድምጽ (Yedel Demts) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ ደግሞ ፡ ደነገጠ ፡ ጠላቴ
አየ ፡ ያደረገውን ፡ በሕይወቴ
ውድቀትና ፡ ሞቴን ፡ ሲጠብቅ
ሰማ ፡ በማለዳ ፡ የድል ፡ ድምጽ
አሸነፈ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሳካለት ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሻገረ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
አልተያዘም ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ

ያመንኩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የተደገፍኩህ
ዘንድሮም ፡ አየሁት ፡ መልካሙን ፡ እጅህን
አላፈርኩም ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ አስቀድሜ
ተሳካልኝ ፡ እንጂ ፡ በነፍስ ፡ በስጋዬ

አዝ፦ ደግሞ ፡ ደነገጠ ፡ ጠላቴ
አየ ፡ ያደረገውን ፡ በሕይወቴ
ውድቀትና ፡ ሞቴን ፡ ሲጠብቅ
ሰማ ፡ በማለዳ ፡ የድል ፡ ድምጽ
አሸነፈ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሳካለት ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሻገረ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
አልተያዘም ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ

የሚታየኝ ፡ ነገር ፡ ሰፋ ፡ ሰፋ ፡ ያለ ፡ ነው
የሚመጣው ፡ ዘመን ፡ የእኔ ፡ የራሴ ፡ ነው
ራዕይና ፡ አላማ ፡ ይዤ ፡ ወጥቻለሁ
አልቆምም ፡ አልቆምም ፡ እገሰግሳለሁ

አዝ፦ ደግሞ ፡ ደነገጠ ፡ ጠላቴ
አየ ፡ ያደረገውን ፡ በሕይወቴ
ውድቀትና ፡ ሞቴን ፡ ሲጠብቅ
ሰማ ፡ በማለዳ ፡ የድል ፡ ድምጽ
አሸነፈ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሳካለት ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
ተሻገረ ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ
አልተያዘም ፡ የሚል ፡ የድል ፡ ድምጽ

ሊረግመኝ ፡ ሲነሳ ፡ ኃይሉን ፡ አሰባስቦ
በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ ተራራ ፡ ላይ ፡ ሆኖ
መጣበት ፡ ጌታዬ ፡ ቀይር ፡ ቃሉን ፡ ብሎ
ሊረግመኝ ፡ የመጣ ፡ ሄደ ፡ መልካም ፡ ብሎ
(ሊረግመኝ ፡ የመጣ ፡ ሄደ ፡ መልካም ፡ ብሎ)

ይህን ፡ ላደረገው ፡ ለጌታ
የታል ፡ ዕልልታ ፡ የታል (፪x)
የታል ፡ ጭብጨባው ፡ የታል (፪x)
የታል ፡ ለጌታ ፡ የታል (፪x)
የታል ፡ ለአምልኮ ፡ የታል
የታል ፡ ዕልልታ ፡ የታል