ያየሁትን (Yayehuten) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወደማን ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ (፪x)
ድምጽህን ፡ ሰምቼ ፡ አንዴ ፡ ተደላድያለሁ
የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሰለቸኝ ፡ ደከመኝ ፡ አታውቅ ፡ እኔ ፡ አይቼሃለሁ
ታዲያ ፡ ከእቅፍህ ፡ ወዴት ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ

አባት ፡ ቢሉት ፡ የደረሰላቸው
ፍቅር ፡ ሚሉት ፡ የቀመሱት ፡ ናቸው
ተስፋ ፡ ጠፍቶ ፡ ተስፋ ፡ የሆናቸው
በተዐምራት ፡ በድንቅ ፡ የመራቸው
አመስግኖ ፡ አይጠግብም ፡ ልባቸው (፪x)

ክበር ፡ ብሎ ፡ ንገሥ ፡ ብሎ (አሜን)
ልዩ ፡ ብሎ ፡ አይጠግብም ፡ ልባቸው (፪x)

ያየሁትን ፡ የሰማሁትን (የሰማሁትን)
እናገራለሁ ፡ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን)
(፪x)
ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና
ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና
ነፃ ፡ አደረገኝ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፈለና

ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ በፍቅርህ ፡ በቤትህ ፡ እኖራለሁ (፪x)
በሚያስተማምነው ፡ ክንድህ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ አርፌአለሁ
በውኃ ፡ ዳር ፡ እንደአለች ፡ ተክል ፡ ፍሬያማ ፡ ሆኛለሁ
የረገጥኩት ፡ ምድር ፡ በአንተ ፡ ሲገዛ ፡ አይቻለሁ
ስምህን ፡ ጠርቼ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ አስነካለሁ

ያየሁትን ፡ የሰማሁትን (የሰማሁትን)
እናገራለሁ ፡ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን)
(፪x)
ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና
ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና
ነፃ ፡ አደረገኝ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፈለና