ማኅተሙን ፡ ፈታ (Mahetemun Feta) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
ጌታችንና ፡ አምላካችን
ክብር ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል
ኃይል ፡ ብርታት ፡ ጥበብ ፡ ሞገስ
ፍቅር ፡ በውስጥህ ፡ ተሞልተሃል (፪x)

መጽሃፉን ፡ ወስደህ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈትተሃል
የሰዉን ፡ ጥያቄ ፡ አንተ ፡ መልሰሃል
ክብር ፡ ይገባሃል (፬x) ፡ ክብር ፡ ይገባሃል (፪x)

ይህን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ (፪x)
አንተን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ
ሥራህን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ

ኃይልህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
ሥምህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
ማዳንህ ፡ ግሩም ፡ ግሩም ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው

ይህን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ (፪x)
አንተን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ
ሥራህን ፡ ያዩ ፡ ዐይኖቼ ፡ ተያዙ ፡ በፍቅርህ ፡ ተማረከች ፡ ነፍሴ

ስለእኔ ፡ የፈሰሰው ፡ የደም ፡ ዋጋ
ስለእኔ ፡ የሞተው ፡ ጌታ
እኔን ፡ ነፃ ፡ አርጐኛል ፡ ከሞት ፡ ከኀጢአት ፡ ዕዳ
ስለእኔ ፡ እርሱ ፡ ተጐዳ (፫x)

ኢየሱስ ፡ ጌታ ፣ ኢየሱስ ፡ ፍቅር
ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፣ ኢየሱስ ፡ ታጋዥ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መሃሪ (፪x)