ካወቅሁት ፡ ጀምሮ (Kaweqhut Jemero) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
እኔ ፡ ያወቅሁት ፡ ካወቅሁት ፡ ጀምሮ
ታሪክ ፡ ሲለውጥ ፡ በአዲስ ፡ አሳምሮ
ሰዎችም ፡ ሲሉ ፡ ሃዘኔን ፡ አስረሳኝ
የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳን

አዝ፦ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ፡ ከእሳት ፡ እያሉ

ማን ፡ ያልወጣ ፡ አለ ፡ ከጭንቅ ፡ ከፍራቱ
አንተን ፡ አስገብቶ ፡ ጌታ ፡ በሕይወቱ
ተዐምረኛ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ የተጣለውን ፡ ታነሳለህ (፫x)
ተአምረኛ ፡ ሃይለእኛ ፡ ነህ ፡ በፍቅር ፡ ልብን ፡ ትይዛለህ

የታሰርኩበትም ፡ ሰንሰለት ፡ ረገፈ
የእስር ፡ ቤቱ ፡ መዝጊያ ፡ ራሱ ፡ ተከፈተ
አዳነኝጌታዬ ፡ መልአኩን ፡ ልኩ
ነፍስም ፡ አልቀረኝ ፡ አይ ፡ አደራረጉ

አዝ፦ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ
እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ፡ ከእሳት ፡ እያሉ

ማን ፡ ያልወጣ ፡ አለ ፡ ከጭንቅ ፡ ከፍራቱ
አንተን ፡ አስገብቶ ፡ ጌታ ፡ በሕይወቱ
ተዐምረኛ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ የተጣለውን ፡ ታነሳለህ (፫x)
ተአምረኛ ፡ ሃይለእኛ ፡ ነህ ፡ በፍቅር ፡ ልብን ፡ ትይዛለህ

እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለ ፡ እያሉ
ወንድሞች ፡ በሆታ ፡ ስራህን ፡ ያወራሉ
እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለ ፡ እያሉ
እህቶች ፡ በዕልልታ ፡ አንተን ፡ ያደንቃሉ
ፍቅርህን ፡ የቀመሱ ፡ በረከትህን ፡ ያዩ
ከውስጥ ፡ ከልባቸው ፡ አንተን ፡ ያከብራሉ
አንተን ፡ ያከብራሉ ፡ አንተን ፡ ያነግሳሉ
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ እያሉ
(፪x)