ጌታ ፡ ተናግሯል (Gieta Tenagrual) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
ሰማይን ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ምድርን ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ ነው
ታዲያ ፡ እኔ ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ
ታዲያ ፡ እኔ ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ ፡ በደስታ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ

እርሱ ፡ ተናግሯል ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ
የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል
ጌታ ፡ ተናግሯል ፡ ቤተሰቤ ፡ ላይ
የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል
ጌታ ፡ ተናግሯል ፡ በሃገሬ ፡ ላይ
የሚቀር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይሆናል

እግዚአብሔር ፡ በማን ፡ ይመሰላል ፡ ከማን ፡ ጋራ ፡ ይወዳደራል
የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነው ፡ ኃይሉ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ጐበዝ ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ ይወድቃሉ ፡ ኃይለኞች ፡ ደግሞ ፡ ይደክማሉ
ጌታን ፡ መመኪያ ፡ ያደረጉ ፡ ሕይወታቸውን ፡ ለርሱ ፡ የሰጡ

ይወጣሉ ፡ ይሮጣሉ ፣ ከቶ ፡ አይደክሙም ፡ ያሸንፋሉ
ከፍታውን ፡ ይይዛሉ
እወጣለሁ ፡ ገና ፣ እሮጣለሁ ፡ ከቶ ፡ አልደክምም ፡ አሸንፋለሁ
ከፍታውን ፡ እይዛለሁ

እይታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ የእኔስ ፡ ኑሮ ፡ ሰማያዊ ፡ ነው
አምኖ ፡ በምድር ፡ አሰማርቶኛል ፡ ማንነቴን ፡ ተርክ ፡ ብሎኛል
ለተጠማ ፡ እርካታ ፡ ለደከመው ፡ ጉልበት ፡ ላዘነው ፡ ደስታ
ይህን ፡ እንደሚሰጥ ፡ ነው ፡ ማውቀው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

ይሄ ፡ ነው ፡ የተጻፈው
ይሄ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ የተባለልኝ (፬x)