Solomon Yirga/Meazayie Neh/Ende Balehamsa Qen
| ርዕስ = እንደ ፡ ባለሃምሳ ፡ ቀን | Title = Ende BaleHamsa Qen | ዘማሪ = ሰለሞን ፡ ይርጋ | Artist = Solomon Yirga | Volume = 2 | አልበም = መዓዛዬ ፡ ነህ | Album = Meazayie Neh | Track = 6 | Year = ፳ ፻ ፫ (2011)
ኧረ ፡ ምን ፡ ይባል ፡ ምን ፡ ይባል ፡ ይህ ፡ ጌታ
እኔ ፡ ምለው ፡ አጣሁ ፡ አስገረመኝ ፡ ጌታ
ምነው ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ባይኖር
ቀንና ፡ ሌሊቱን ፡ እልል ፡ ሲባል ፡ ሲመለክ ፡ ቢታደር
በህልውናው ፡ ውስጥ ፡ እልም ፡ ጥፍት ፡ ስምጥ ፡ ብሎ ፡ ማደር
አዝ፦ እንደ ፡ ባለሃምሳ ፡ ቀን ፡ እንደ ፡ መጀመሪያው
ና ፡ ደግመህ ፡ በሕይወቴ
ና ፡ ደግመህ ፡ በሕይወቴ ፡ ሙላኝ ፡ በመንፈስህ
ልሂድ ፡ ወደሰማይ ፣ ልሂድ ፡ ወደሰማይ (፪x)
ከአቻምናው ፡ የአምናው ፡ የዘንድሮው ፡ ባሰ
በተጠጋሁት ፡ ቁጥር ፡ ሕይወቴ ፡ እየራሰ ፡ እየረሰረሰ
ህልውናውን ፡ ወደድኩ ፡ ከሁሉ ፡ የበለጠ
መገኘቱን ፡ ናፈቅሁ ፡ ከሁሉ ፡ የበለጠ
ኢየሱሴን ፡ ወደድኩ ፡ ከሁሉ ፡ የበለጠ
ኢየሱሴን ፡ ናፈቅሁ ፡ ከሁሉ ፡ የበለጠ
አዝ:- እንደ ፡ ባለሃምሳ ፡ ቀን ፡ እንደ ፡ መጀመሪያው
ና ፡ ደግመህ ፡ በሕይወቴ
ና ፡ ደግመህ ፡ በሕይወቴ ፡ ሙላኝ ፡ በመንፈስህ
ልሂድ ፡ ወደሰማይ ፣ ልሂድ ፡ ወደሰማይ (፪x)
ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አለህ
ቢቀዳ ፡ ቢቀዳ ፡ እንደማያልቅ ፡ እንደመልካም ፡ ምንጭ ፡ ነህ
ምን ፡ ብዬ ፡ ልግለጽህ (የእኔ ፡ ጌታ) ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገር
እጅጉን ፡ ድንቅ ፡ ነህ (፪x)
ዋላ ፡ የውኃ ፡ ምንጭ ፡ ሁሌ ፡ እንደምትናፍቅ (፪x)
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች ፡ አንተን ፡ ፈለገችህ (፪x)
ማለዳ ፡ ተነስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ አለችህ