በማለዳ ፡ ምሥጋናዬ (Bemaleda Mesganayie) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬ ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬዬn
ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ ወደ ፡ ፊትህ
ቤትህን ፡ ይሙላው ፡ ያውድልህ (፪x)

ሰዎች ፡ ሰውን ፡ አይተው ፡ ያፈገፍጋሉ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ ጥለው ፡ ይሄዳሉ
እኔ ፡ ግን ፡ ባሰብኝ ፡ ጨመረብኝ ፡ ፍቅሩ
አልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከድንበሩ
አልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከድንበሩ
እልሻም ፡ ለሰከንድ ፡ መውጣት ፡ ከክልሉ
(፪x)

አዝ፦ በማለዳ ፡ ምሥጋናዬ ፡ በሌሊትም ፡ ዝማሬዬ
ይዤ ፡ ልቅረብ ፡ ወደ ፡ ፊትህ
ቤትህን ፡ ይሙላው ፡ ያውድልህ (፪x)

በምድር ፡ እስካለሁ ፡ እኔ ፡ እናገራለሁ
ብዙ ፡ ተደርጐልኝ ፡ ብዙ ፡ አይቻለሁ
የማይገባኝን ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ
ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ እላለሁ
ጐንበስ ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ አመልከዋለሁ (፬x)

እኔስ (፬x) ፡ እኔስ ፡ እንደገና ፡ ቃልን ፡ እገባለሁ
ሃሳብህን ፡ ይዤ ፡ ሃሳቤን ፡ እጥላለሁ
የወደድከው ፡ ይሁን ፡ አባ ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ እታዘዛለሁ
አንተን ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)