አሸጋገረን (Ashegageren) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አሸጋገረን ፡ ጌታ ፡ አሸጋገረን
ከኋላችን ፡ አየነው ፡ ቀይ ፡ ባሕርን
በጌታዬ ፡ ዐይን ፡ ለካ ፡ ሁሉም ፡ ቀላል ፡ ነው
ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ የእጁ ፡ ስራ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ምድር ፡ ሰማይ ፡ ቢነዋወጥ
የጌታዬ ፡ ቃል ፡ ፍፁም ፡ አይለወጥ
ዘንድሮ ፡ በዐይኔ ፡ ያየሁት ፡ ይህን ፡ ነው
ያመንኩት ፡ ጌታ ፡ ተዐምረኛ ፡ ነው

የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የይሳቅ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የያቆብ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የሚያድን ፡ የሚታደግ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ (፪x) ፡ ዛሬም ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ
አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ

ከሰማይ ፡ ጠል ፡ ወረደ ፡ ከምድር ፡ ስብ
የያእቆብ ፡ አምላክ ፡ ሰማን ፡ መለሰልን
በበረሃ ፡ ወንዞችን ፡ አዘጋጅቶልን
አረካን ፡ ጌታ ፡ አረሰረሰን (፪x)

አዝ፦ ምድር ፡ ሰማይ ፡ ቢነዋወጥ
የጌታዬ ፡ ቃል ፡ ፍፁም ፡ አይለወጥ
ዘንድሮ ፡ በዐይኔ ፡ ያየሁት ፡ ይህን ፡ ነው
ያመንኩት ፡ ጌታ ፡ ተዐምረኛ ፡ ነው

የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የይሳቅ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የያቆብ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
የሚያድን ፡ የሚታደግ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ) (፪x)
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ አለ (አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ)
አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ (፪x) ፡ ዛሬም ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ
አለ ፡ ዛሬም ፡ አለ