አስቤ ፡ አስቤ (Asebie Asebie) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
አስቤ ፡ አስቤ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ብዬ (፪x)

ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
እጄን ፡ አንስቼ ፡ ከማምለክ ፡ ሌላ
ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
ዕድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ከመስጠት ፡ ሌላ

አልሜ ፡ አልሜ (፪x)
ለፍቅሩ ፡ ትርጉም ፡ ልሰጠው ፡ ብዬ
አልሜ ፡ አልሜ (፪x)
ላደረገው ፡ ምላሽ ፡ ልሰጠው ፡ ብዬ

ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
እጄን ፡ አንስቼ ፡ ከማምለክ ፡ ሌላ
ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
ዕድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ከመስጠት ፡ ሌላ

ይጀመራል ፡ እንጂ ፡ አይጨረስም
እግዚአብሔር ፡ የሰራው ፡ ከቶ ፡ አያልቅም
በየዘመናቱ ፡ ድንቅ ፡ ያደርጋል
ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነው
(፪x)

ትልቅ ፡ ነው ፡ መጀመሪያ ፡ የለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ መጨረሻ ፡ የለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ ሚመስለው ፡ የሌለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪x)

አስቤ ፡ አስቤ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ብዬ
አስቤ ፡ አስቤ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ብዬ (፪x)

ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
እጄን ፡ አንስቼ ፡ ከማምለክ ፡ ሌላ
ግን ፡ አጣሁልህ ፡ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ
ዕድሜ ፡ ዘመኔን ፡ ከመስጠት ፡ ሌላ

ጨለማው ፡ ተገፍፎ ፡ ብርሃን ፡ ሲሆን
ተራራውም ፡ ቀልጦ ፡ ሜዳ ፡ ሲሆን
ያልነበረው ፡ ሲኖር ፡ አይቻለሁ
ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነው
(፪x)

ትልቅ ፡ ነው ፡ መጀመሪያ ፡ የለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ መጨረሻ ፡ የለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ ሚመስለው ፡ የሌለው
ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው (፬x)