አሳርፈኸኛል (Asarefehegnal) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(Track)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
እንዲህ ፡ አልነበረም ፡ ታሪኬ
አንተ ፡ ሳትገባ ፡ በሕይወቴ (፪x)
ውስጤን ፡ ስትነካው ፡ ታወቀ ፡ በፊቴ
አሳርፈኸኛል ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ
አመሰግናለሁ ፡ ተመስገን ፡ አባቴ (፪x)
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል
ዘለዓለም ፡ በቤትህ ፡ ያኖሩኛል (፪x)

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው ፡ የሚያሳጣኝ ፡ አንድም ፡ ነገር ፡ የለም
በለመለመው ፡ መስክ ፡ ይመራኛል ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ያሳድረኛል
ነፍሴን ፡ መለሳት ፡ ስለስሙ ፡ በጽድቅ ፡ መንገድ ፡ መራኝ
በሞት ፡ መሃከል ፡ እንኳን ፡ ብሄድ
እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነውና ፡ ክፉን ፡ አልፈራም ፡ እኔ ፡ አልፈራም

ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ የሆነው
ይህ ፡ ነው ፡ አይባልም ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ ነፃ ፡ እንድሆን ፡ ሁሉን ፡ ሆኖልኛል
ሞቴንም ፡ በሞቱ ፡ ጌታዬ ፡ ለውጧል (፪x)

አንተ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ ፡ ውበት ፡ ደም ፡ ግባቴ
አመሰግናለሁ ፡ ተመስገን ፡ አባቴ (፪x)
ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል
ዘለዓለም ፡ በቤትህ ፡ ያኖሩኛል (፪x)