አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋር (Ale Kenie Gar) - ሰለሞን ፡ ይርጋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ይርጋ
(Solomon Yirga)

Solomon Yirga 2.jpeg


(2)

መዓዛዬ ፡ ነህ
(Meazayie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ይርጋ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Yirga)

 
የትላንቱን ፡ ነገር ፡ ጌታዬ ፡ ካስረሳኝ
አምናን ፡ አሳልፎ ፡ ለዛሬ ፡ ካበቃኝ
ስለነገው ፡ ደግሞ ፡ አምኜ ፡ ልናገር
አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከቶ ፡ የማይደክመው ፡ ስለእኔ ፡ ሚናገር (፫x)
አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከቶ ፡ የማይደክመው ፡ ስለእኔ ፡ ሚናገር (፪x)

አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
አለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አለ
አለ ፡ የሚመራኝ ፡ አለ
አለ ፡ የሚራራልኝ ፡ አለ
አለ ፡ አለ (፪x)

እረኛ ፡ እንደሌለው ፡ አልቅበዘበዝም
በሚነፍሰው ፡ ንፋስ ፡ አልነዋወጥም
መሠረቴ ፡ ጽኑ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ
የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተናገረውን/የተናገረኝ ፡ ሲያደርግ ፡ አይቻለሁ (፪x)
የማመልከው ፡ አምላክ ፡ የተናገረኝ ፡ ሲያደርግ ፡ አይቻለሁ (፪x)

አለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
አለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አለ
አለ ፡ የሚመራኝ ፡ አለ
አለ ፡ የሚራራልኝ ፡ አለ
አለ ፡ አለ (፪x)

እንዳለኝ ፡ እኖራለሁ ፡ እንደተናገረኝ
የምትረግጠው ፡ ምድር ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ እንዳለኝ (፪x)

እንደንስር ፡ በሰማይ ፡ በከፍታ ፡ እበራለሁ
እንደአንበሳ ፡ ደቦል ፡ በምድር ፡ እመላለሳለሁ
እመላለሳለሁ (፫x) ፡ ከልካዬ ፡ ኧረ ፡ ማነው (፪x)