ላምጣልህ ፡ ምሥጋና (Lamtaleh Mesgana) - ሰለሞን ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሰለሞን ፡ ነጋሽ
(Solomon Negash)

Solomon Negash 1.jpg


(1)

ተጠምተናል
(Tetemtenal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሰለሞን ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Solomon Negash)

ልትሰራ ፡ አስበህ ፡ ስትመጣ ፡ ወደ ፡ እኔ
አንተ ፡ ያየኸውን ፡ ስታሳየኝ ፡ በዓይኔ
ምህረትህ ፡ ሲለየኝ ፡ ለከበረው ፡ ሥራ
ውስጤ ፡ ተደነቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ (፪x)

ቆይ ፡ ምኔን ፡ ደስ ፡ ብሎ ፡ የቱስ ፡ እኔነቴ
ወደ ፡ እኔ ፡ ያመጣህ ፡ ልታሰገባህ ፡ ወደ ፡ እኔ
ይሄ ፡ አልበቃህ ፡ ብሎ ፡ በክብርህ ፡ እንድትሰራ
ፍቅርህ ፡ የመረተኝ ፡ ባንተው ፡ እንድጠራ

አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ
ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ
ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ
ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ

ፍቅር ፡ ግድ ፡ ብሎህ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድከኝ
ለሹመት ፡ ለክብር ፡ ብለህ ፡ የወሰንከኝ
ኃጢአት ፡ ያጠፋህ ፡ ድካሜን ፡ የሻረከው
ውልታህ ፡ በዝቶብኝ ፡ ፊትህ ፡ መጥቼአለሁ

ይኸው ፡ አድናቆቴ ፡ ለክብርህ ፡ ምሥጋና
ይኸው ፡ መገዛቴ ፡ ወደኸኛልና
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ የከንፈሬ ፡ ፍሬ
ኧረ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያበቃኝ ፡ ለዛሬ

ልትሰራ ፡ አስበህ ፡ ስትመጣ ፡ ወደ ፡ እኔ
አንተ ፡ ያየኸውን ፡ ስታሳየኝ ፡ በዓይኔ
ምህረትህ ፡ ሲለየኝ ፡ ለከበረው ፡ ሥራ
ውስጤ ፡ ተደነቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ (፪x)

አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ
ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ
ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ
ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ በመንፈስህ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታቴ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እስካሁን ፡ የሆነው ፡ በሕይወቴ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሠላም ፡ ይሰማኛል ፡ ነገዬን ፡ ሳሰበው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ በፊቱ ፡ አልሰጋም ፡ ተስፋዬ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው

አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ
ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ
ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ
ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ