ልዩ ፡ ነህ (Leyu Neh) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Lyrics.jpg


(Volume)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Singles)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

በፈለግኩሀ ፡ ቁጥር ፡ አገኝሃለሁ
ባገኘሁህ ፡ ቁጥር ፡ ይበልጥ ፡ እወድሃለሁ

እወድሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ እወድሃለሁ(፪)

ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አምላኬ(፪)
እንዳንተ ፡ አጣሁኝ ፡ ፈልጌ(፬)

ብዙ ፡ ይቅር ፡ ያልከው ፡ ብዙ ፡ ይወድሃል
ጥቂት ፡ የተውክለት ፡ እንደዛው ፡ ይኖራል
እግርህን ፡ በእንባዬ ፡ እያረሰረስኩ
ሽቶዬን ፡ ልቀባ ፡ . (1) .


አባቴ ፡ ለእኔ ፡ ያረግኸው ፡ ብዙ ፡ ነው
የምሥጋና ፡ አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ይኸውና ፡ ማደርያህን ፡ ያውደው
አምልኮዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ያጥለቅልቀው

አባቴ ፡ ለእኔ ፡ ያረግኸው ፡ ብዙ ፡ ነው
የምሥጋና ፡ አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ይኸውና ፡ ማደርያህን ፡ ያውደው
ለውለታህ ፡ መታሰብያው ፡ ይሄ ፡ ነው

እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለህም ፡ እንደ ፡ ራስህ ፡ እንጂ
ወደ ፡ አንተ ፡ የመጡትን ፡ አታወጣም ፡ ከደጅ
አትለዋወጥም ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ
ወረትን ፡ አታውቅም ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ

እኔማ ፡ ተባረክ ፡ ልበል ፡ እንጂ
ሲታወቀኝ ፡ እንደያዘኝ ፡ መልካም ፡ እጅህ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያረግኸው ፡ ብዙ ፡ ነው
የምሥጋና ፡ አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው

ልጄ ፡ ሆይ ፡ ብረሳሽ ፡ ቀኜ ፡ ትርሳኝ ፡ ብለህ
ኪዳንህን ፡ አጸናህ ፡ በራስህ ፡ ተማምለህ
ሰማዩን ፡ ዝቅ ፡ አርገህ ፡ አየሁህ ፡ ስትመጣ
እኔን ፡ መጥተህ ፡ ማየት ፡ ባለህበት ፡ ቦታ

አባቴ ፡ ለእኔ ፡ ያረግኸው ፡ ብዙ ፡ ነው
የምሥጋና ፡ አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ይኸውና ፡ ማደርያህን ፡ ያውደው
አምልኮዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ያጥለቅልቀው

አባቴ ፡ ለእኔ ፡ ያረግኸው ፡ ብዙ ፡ ነው
የምሥጋና ፡ አልባስጥሮሴን ፡ ልስበረው
ይኸውና ፡ ማደርያህን ፡ ያውደው
ለውለታህ ፡ መታሰብያው ፡ ይሄ ፡ ነው

በፈለግኩሀ ፡ ቁጥር ፡ አገኝሃለሁ
ባገኘሁህ ፡ ቁጥር ፡ ይበልጥ ፡ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ እወድሃለሁ(፪)

ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አምላኬ(፪)
እንዳንተ ፡ አጣሁኝ ፡ ፈልጌ(፬)

እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ(፫)
ኢየሱስ ፡ እወድሃለሁ