From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ
ላማ ፡ ሰበቅታኒ [1][2]
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ
ዎይ (፲፫x)
ይዘዉህ ፡ ሲሄዱ ፡ እንደሚታረድ ፡ በግ
ዝም ፡ ብለህ ፡ እየሄድክ ፡ አንዳች ፡ ሳትሟገት
ማነኝ ፡ ለመሆኑ ፡ እንዴት ፡ እወደድከኝ
ከክብር ፡ ላይ ፡ ወርደህ ፡ የተዋረድክልኝ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ
ፊቴ ፡ ድቅን ፡ ይላል ፡ የእሾህ ፡ ጉንጉኑ
የጅራፉ ፡ ብዛት ፡ የገላ ፡ ሰንበሩ
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ላማ ፡ ሰበቅታኒ [1][2]
ብለህ ፡ ስትጨነቅ ፡ ስለእኔ ፡ ስትማቅቅ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ጻድቅ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ንጹህ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ
ጻድቅ ፡ ሰው ፡ በመስቀል ፡ እርቃኑን ፡ አደረ
ስለ ፡ ኃጥያተኞች ፡ ደሙን ፡ አፈሰሰ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ
ዎይ (፲፫x)
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ
|
- ↑ 1.0 1.1 ማቴዎስ ፳፯ ፡ ፵፮ (Matthew 27:46)
- ↑ 2.0 2.1 ማርቆስ ፲፭ ፡ ፴፬ (Mark 15:34)