የእኔ ፡ ምስጋና (Yenie Mesgana) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

የእኔ ፡ ምሥጋና
ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና (፪x)

ወይ ፡ ዘንቦ ፡ ላይዘንብ ፡ ወይ ፡ ጥሎ ፡ ላይጥል
መብረቁ ፡ ሲያስፈራ ፡ ሲል ፡ ብልጭ ፡ ድርግም (፪×)
ነጐድጓዱ ፡ ታሞ ፡ ጠብ ፡ እንኳን ፡ ካላለ
ዝናብ ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ቤቱ ፡ ከዋለ ፡ ተታለለ
ግርግር ፡ ባይኖር ፡ ሙዚቃ ፡ ባልሰማ
የነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ዙፋኑ ፡ ይሰማ
ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና

የእኔ ፡ ምሥጋና
ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና

እህሉ ፡ ሊበላሽ ፡ ዘንቦበት ፡ በረዶ
እያለ ፡ ሲያወራ ፡ ካሁን ፡ አሁን ፡ ወርዶ ፡ በረዶ
ጉሙ ፡ ሲያጉረጐርም ፡ መጣሁኝ ፡ እያለ
ደመናው ፡ ሰንጥቆት ፡ ፀሐይ ፡ ብቅ ፡ ካለ ፡ ተታለለ
ዝም ፡ ብዬ ፡ የምጮህ ፡ እንዲያው ፡ ባዶ ፡ ሜዳ
አይደለሁም ፡ እኔስ ፡ ሞልቶኛል ፡ ምሥጋና
ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና

ምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x)
እሰዋለሁ ፡ ለጌታዬ ፡ ለአምላኬ
ይገባዋልና ፡ በከፍታ ፡ በዝቅታ
አምልኮዬን ፡ አቀርባለሁ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ በደስታ

ምሥጋና ፡ ምሥጋና (፪x)
ለጌታዬ ፡ ለታደገኝ ፡ ለአዳነኝ
ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ እያልኩኝ ፡ እየሰገድኩ ፡ እያመለኩ
ፊቱ ፡ ብወድቅ ፡ ባደንቀው ፡ ባሞግሰው ፡ ለእርሱ ፡ አይበቃም

የእኔ ፡ ምሥጋና
ዝናብ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
ውኃ ፡ እንደሌለው ፡ ደመና
አይደለም ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና (፪x)