ታሪኬ ፡ የጀመረው (Tarikie Yejemerew) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ታሪኬ ፡ የጀመረው (፫x)
በመስቀሉ ፡ ሥር ፡ ነው (፪x)

የተነሳበትን ፡ የማያውቅ ፡ የሚደርስበትን ፡ አያውቅም
የተወለድኩ ፡ ቀን ፡ ታሪኬ ፡ እንደተጀመረ ፡ እንኳን ፡ ባውቅም
ከዚህ ፡ ዕውቀት ፡ ልኩ ፡ ያለፈ ፡ ሌላ ፡ ዕውቀት ፡ ተገልጦልኛል
የታሪኬ ፡ ጅምር ፡ መነሻው ፡ ከመስቀሉ ፡ ግርጌ ፡ ሆኖኛል

ያወኩት ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ ጌታዬ
ስቀበለው ፡ እንደግል ፡ አዳኜ
ስመዘገብ ፡ በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ
ጀማመረ ፡ ታሪኬ ፡ እዚያ ፡ ላይ (፪x)

ታሪኬ ፡ የጀመረው (፫x)
በመስቀሉ ፡ ሥር ፡ ነው (፪x)

ሰው ፡ ሞቶ ፡ ሲሸኝ ፡ ወደ ፡ ቀብር ፡ ሁሉም ፡ አልቅሶ ፡ ይሸኘዋል
ቀብረው ፡ ሲመለሱ ፡ ታሪኩን ፡ በቃ ፡ ሁሉም ፡ ይዘነጉታል
የእኔ ፡ ግን ፡ ከዚህ ፡ የተለየ ፡ ነው ፡ ታሪኬ ፡ እዛ ፡ ላይ ፡ አያበቃም
ወደ ፡ ዘለዓለማዊው ፡ ሃገሬ ፡ ጭራሽ ፡ ወደ ፡ ሌላ ፡ ይሻገራል

ነፍሴ ፡ ከሥጋዬ ፡ ስትለያይ
ወደ ፡ ጌታዋ ፡ ስትሄድ ፡ ወደ ፡ ላይ
ሌላ ፡ ታሪክ ፡ ደግሞ ፡ ጀምራለሁ
ወደ ፡ አዳነኝ ፡ ጌታ ፡ እሄዳለሁ (፪x)

ታሪኬ ፡ የሚቀጥለው (፫x)
ከሞት ፡ ባሻገር ፡ ነው (፪x)