From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ሰው ፡ አነሰ ፡ አይባል ፡ እከሌ ፡ ነኝ ፡ ይላል
ከስሙ ፡ አስቀድሞ ፡ ያለ ፡ የሌለ ፡ ነገር ፡ ጨማምሮ ፡ ይናገራል
ሥራህስ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ቢጠይቁት
አሳምሮ ፡ ያወራል ፡ ያብራራል ፡ ከሰሙት
ለመጥምቁ ፡ ዮሐንስ ፡ ኢሄ ፡ እድል ፡ ደረሰው
አንተ ፡ ማነህ ፡ ብሎ ፡ ብዙ ፡ ህዝብ ፡ ጠየቀው
እንዲህ ፡ ሲል ፡ መለሰ ፡ ስለ ፡ ማንነቱ
ሳያፍር ፡ ገለጠ ፡ እውነትን ፡ ከውሸቱ
እኔ ፡ ጠራጊ ፡ ነኝ ፣ ድምጽ ፡ ነኝ ፣ ምጮኸው
መንገድ ፡ የማዘጋጅ ፡ ከኋላ ፡ ሄዳለሁ
አይደለሁም ፡ ኤልያስ ፡ ከነብያቶች ፡ አንዱ
የማመቻች ፡ ነኝ ፡ ጥርጊያ ፡ ለመንገዱ
አላቸው ፡ መልሶ ፡ ራሱን ፡ አሳንሶ
የጫማውን ፡ ጥፍር ፡ ልፈታ ፡ የማይገባኝ
ከእርሱ ፡ አንሳለሁኝ
እኔ ፡ ላንስ ፡ ይገባል ፡ እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ይበልጣል
እኔ ፡ በውኃ ፡ ሳጠምቅ ፡ በእሳት ፡ ያጠምቃል
እርሱ ፡ ከእኔ ፡ ይበልጣል[1][2]
እንዲህ ፡ ነው ፡ እንግዲህ ፡ ትህትና
እንዲህ ፡ ነው ፡ እንግዲህ ፡ ዝቅ ፡ ማለት (፪x)
ራስን ፡ ማወቅ ፡ ማንነትን
ሰው ፡ መሆንን ፡ መረዳትን
ያበዛዋል ፡ መዋረድን
ሒሳቡ ፡ ደግሞ ፡ ኢሄ ፡ ነው
ዝቅ ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ የሚለው (፪x)
እኔ (፮x) ፡ ባልኩኝ ፡ ቁጥር
እወጣለሁኝ ፡ ካለሁበት ፡ አጥር
እኔ (፮x) ፡ ያልኩኝ ፡ ለታ
ያበቃልኛል ፡ የማታ ፡ የማታ
እኔነቴ ፡ መድከሚያዬ
እኔነቴ ፡ መውደቂያዬ
እኔነቴ ፡ መወጫዬ
እኔነቴ ፡ መቃብሬ
ስንቱ ፡ ተቀበረ ፡ በእኔነት ፡ መቃብር
ትንሳዔ ፡ ያምጣለት ፡ ትሁቱ ፡ እግዚአብሔር (፪x)
እንደ ፡ እንጀራ ፡ አይለመን ፡ ትህትና
መለወጥ ፡ ነዉ ፣ መወሰን ፡ ነዉ ፣ የሚያስፈልገዉ
በትዕቢት ፡ ከጋሉ
እኔነቴ ፡ መድከሚያዬ
እኔነቴ ፡ መውደቂያዬ
እኔነቴ ፡ መወጫዬ
እኔነቴ ፡ መቃብሬ
|
- ↑ ሉቃስ ፫ ፡ ፲፮ (Luke 3:16)
- ↑ ማርቆስ ፩ ፡ ፯ (Mark 1:7)