እንዲህ ፡ አይደረግም (Endih Ayderegem) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

የእኔን ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ የፍጥረቴን ፡ ሚስጥር
የደመነፍስ:ኑሮን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚተረትር
የታረደለኝ ፡ በግ ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ ሕይወት ፣ ያለኝ ፡ ነኝ
እኔም ፡ ዝቅ ፡ በዬ ፡ ልስገድለት ፡ ለእርሱ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ

ምሥጋና (፬x) ነው ፡ ያለኝ (፪x)

ተከተይኝ ፡ አለኝ ፡ ትምክቴን ፡ አስጥሎ
የዓለም ፡ አይደለሽም ፡ አንቺ ፡ የእኔ ፡ ነሽ ፡ በሎ
አክብሮት ፡ አምልኮ ፡ ለሌላው ፡ ለመስጠት
ጉልበቶቼ ፡ ታጥፈው ፡ ሊንቀጠቀጡለት

እንዲህ ፡ አይደረግም (፪x)
ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ማንንም ፡ አይመስልም (፪x)

ያልሳሳ ፡ ገበታን ፡ ጌታዬ ፡ አዘጋጅቶ
ከሕይወት ፡ ቃል ፡ ማዕድ ፡ መንፈሴን ፡ አርክቶ
እንዳዜም ፡ ካበቃኝ ፡ በሕያዋን ፡ ምድር
ልሰግድ ፡ ይገባኛል ፡ ከንጉሡ ፡ እግር ፡ ሥር

ይገባኛል (፪x)
አምላኬ ፡ እኮ ፡ እኔን ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ አርጐኛል (፪x)

ከምድራዊው ፡ ኑሮ ፡ ያለፈ ፡ አለ ፡ ብሎ
የሞተልኝ ፡ ጌታ ፡ የእኔን ፡ እዳ ፡ ከፍሎ
ክርስቶስን ፡ ለበስኩ ፡ እንዴት ፡ አምሮብኛል
ክብሬና ፡ ሞገሴን ፡ ማን ፡ ያወልቅብኛል

እንዲህ ፡ አይደረግም (፪x)
ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ማንንም ፡ አይመስልም (፪x)

የእኔን ፡ ሰው ፡ መሆን ፡ የፍጥረቴን ፡ ሚስጥር
የደመነፍስ:ኑሮን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚተረትር
የታረደለኝ ፡ በግ ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ ሕይወት ፣ ያለኝ ፡ ነኝ
እኔም ፡ ዝቅ ፡ በዬ ፡ ልስገድለት ፡ ለእርሱ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ

ምሥጋና (፬x) ነው ፡ ያለኝ
ዕልልታ (፬x) ነው ፡ ያለኝ (፪x)