እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው (Endiet Yale Feqer New) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ስለ ፡ ጻድቅ ፡ ሰው ፡ የሚሞት ፡ መቼም ፡ ቅርብ ፡ ይገኝ
እንዴት ፡ ተገኘ ፡ ብዬ ፡ አያስደንቀኝ
ስለ ፡ ቸር ፡ ሰው ፡ ቢሆን ፡ እንደዚሁ ፡ ነኝ ፡ እኔ
ጊዜዬን ፡ በዚህ ፡ አልፈጅም ፡ ለምኔ ፡ ለምኔ
አንድ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ እኔን ፡ ያስደነቀኝ
ደካማ ፡ እያለሁ ፡ ሳላውቀዉ ፡ ያወቀኝ
ሃጥያት ፡ ያራቀኝ ፡ ከመንገድ ፡ አውጥቶ
ኢየሱስ ፡ መለሰኝ ፡ ሞቴን ፡ ሁሉ ፡ ሞቶ ፡ አሃ

አዝ፦ እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው
እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፪x)

በአንዷ ፡ አለመታዘዝ ፡ ብዙዎች ፡ ኃጥያተኛ ፡ ሆኑ [1]
ከዲያብሎስ ፡ ጋራ ፡ ገሃነም ፡ ሊጣሉ
በኢየሱስ ፡ መታዘዝ ፡ ከፍርድ ፡ አምልጠናል [2]
የመንግሥተ ፡ ሠማይ ፡ ወራሽ ፡ አድርጐናል

አዝ፦ እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው
እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፪x)

ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያለው ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል
ለእኔ ፡ ባረገው ፡ ነገር ፡ ልቤ ፡ ተሸንፏል
የፍቅርንም ፡ ሚስጥር ፡ ያወኩት ፡ በእርሱ ፡ ነው
አቀብት ፡ ዳገቱን ፡ የወጣዉ ፡ ለእኔ ፡ ነው
በደሙ ፡ ተድቄ ፡ ከቁጣ ፡ ድኛለሁ
ጠላትነት ፡ ቀርቶ ፡ ወገን ፡ ተብያለሁ
ሰላሙን ፡ ሰብኮኛል ፡ የሰላም ፡ አለቃ
የጭንቀቱ ፡ ዘመን ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አበቃ ፡ አሃ

አዝ፦ (እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው)
እንዴት ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ንፍስን ፡ የሚያሰጠው
እንዴት ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያስወደው (፬x)

  1. ዘፍጥረት ፫ ፡ ፮ (Genesis 3:6)
  2. ማርቆስ ፲፭ ፡ ፳፩ - ፵፩ (Mark 15:21-41)