From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኢየሱስን ፡ አምኖ ፡ የሕይወቱ ፡ ጌታ ፡ ንጉሱ ፡ ያረገ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ጌታን ፡ በማመኑ ፡ እንደ ፡ ሃይማኖት ፡ ከጂ ፡ አርጐ ፡ የተቆጠረ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ቀድሞ ፡ ከነበሩት ፡ ከባልንጀሮቹ ፡ ተለይቶ ፡ ሄደ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ላመነበት ፡ ነገር ፡ አንገቱን ፡ ለካራ ፡ ሊሰጥ ፡ የጨከነ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x)
በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው
መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው
ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው
ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው
ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው
(ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤይ)
ሌሎች ፡ እንዲድኑ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል ፡ ይዞ ፡ የተጓዘ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
በተሰጠው ፡ መክሊት ፡ ፀጋ ፡ እየሰራ ፡ ብዙ ፡ ያተረፈ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
በስሜቱ ፡ ሳይሆን ፡ በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ውሳኔ ፡ ወሰነ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
በዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ለሚገኘው ፡ አክሊል ፡ ሲልም ፡ ተሯሯጠ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x)
በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው
መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው
ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው
ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው
ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው
(ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ)
ብዙ ፡ ምርጫ ፡ እያለው ፡ አምላኬ ፡ መረጠው ፡ ይሻለኛል ፡ ያለ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ደስታው ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ እንጂ ፡ በዚች ፡ ዓለም ፡ ፈጽሞ ፡ ያልሆነ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ቃል ፡ እየተሞላ ፡ በከበበው ፡ ችግር ፡ ላይ ፡ እየመዘዘ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ድል ፡ በድል ፡ የሚሄድ ፡ ድካሙን ፡ አራግፎ ፡ ቆርጦ ፡ የተጓዘ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x)
በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው
መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው
ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው
ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው
ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው
(ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ)
ሰው ፡ ሲያስቀይመው ፡ ምህረትና ፡ ይቅርታ ፡ ለሁሉ ፡ ያረገ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
በቀል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ለፍቅር ፡ የኖረ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ህሊናው ፡ የጸዳ ፡ በሰዎች ፡ ጉዳይ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ፡ ያልፈተፈተ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ሁሉን ፡ ሰው ፡ የሚያውቀው ፡ በክርስቶስ ፡ ብቻ ፡ በሌላ ፡ ያልሆነ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x)
በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው
መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው
ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው
ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው
ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው
(ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ)
ምሥጋና ፡ ለመስጠት ፡ መስዕዋት ፡ ለማቅረብ ፡ ወደኋላ ፡ ያላለ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ከማንም ፡ ከምንም ፡ አምላኩን ፡ ለማክበር ፡ እራሱን ፡ የሰጠ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ውለታ ፡ የማይረሳ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራቱን ፡ ለሁሉ ፡ የነገረ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ)
ሁልጊዜ ፡ ምሥጋና ፡ ከአፉ ፡ የማይጠፋ ፡ ዕልልታን ፡ ያወቀ
(ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ)
አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x)
በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው
መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው
ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው
ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው
ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ
መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው
(ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ)
|