አንሰዋም (Anasewam) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ሆ (፰x)

ህዝቡን ፡ ከባርነት ፡ ፈልቅቆ ፡ ያወጣ
ከድንጋይ ፡ ላይ ፡ ውኃን ፡ አፍልቆ ፡ ያጠጣ
በመሪባ ፡ ውኃ ፡ ያረሰረሳቸው
በሲና ፡ ተራራ ፡ ያነጋገራቸው
አምላካችን ፡ እርሱ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

እግዚአብሔርን ፡ እንወደዋለን (፬x)

ሙዚቃውን ፡ ስትሰሙ ፡ ለቆመው ፡ ለምስጉን
ለአምላኬ ፡ ወድቃችሁ ፡ ስገዱ ፡ ሲባሉ
እንኳንስ ፡ ሊሰግዱ ፡ ቢንቀለቀል ፡ ቶኑ
ፈፁም ፡ ፍንክች ፡ አይሉም ፡ ሶስቱም ፡ ከጨከኑ
ከአምላካቸው ፡ ሌላ ፡ ለማንም ፡ አይሰግዱ [1]

ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ አናውቅም
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አናመልክም
ለአምላካችን ፡ እንሰግድለታለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንሰዋለታለን

አንሰዋም ፡ ለባዳን ፡ አማልክት
አንሰግድም ፡ ለሠማይ ፡ ሠራዊት
ስግደትን ፡ ስግደት ፡ ለሚገባው
ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ገና ፡ ያኔ ፡ ገና ፡ ሠማይ ፡ ምድርን ፡ ሲሰራ (ኡ ፡ ኦ ፡ ኡ ፡ ኦ)
ቀላያትን ፡ ሲቀድ ፡ ብርሃንን ፡ ሲያበራ (ኡ ፡ ኦ ፡ ኡ ፡ ኦ)
ይሁን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ሁሉ ፡ ለሆነለት
ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ፡ ለፍጥረታት ፡ አባት

ለአምላካችን ፡ ለእርሱ ፡ ለፈጠረን ፡ ጌታ
ዘለዓለም ፡ ይድረሰው ፡ ክብርም ፡ ምሥጋና (፪x)

ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እናመልከዋለን
ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እንሰግድለታለን (፬x)

አንሰዋም ፡ ለባዳን ፡ አማልክት
አንሰግድም ፡ ለሠማይ ፡ ሠራዊት
ስግደትን ፡ ስግደት ፡ ለሚገባው
ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እናመልከዋለን
ሆ ፡ ብለን ፡ እንሄዳለን ፡ እንሰግድለታለን (፬x)

  1. ዳንኤል ፫ (Daniel 3)