From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሃፍረት ፡ አስቀርቅሮ ፡ አንገቴ ፡ ላይ ፡ ቀና
የበደሌ ፡ ቀንበር ፡ በላዬ ፡ ባሰና
በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ ባፈሰስከው ፡ ደምህ
ድፍረት ፡ ሆኖልኛል ፡ እንድቆም ፡ በፊትህ
አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x)
ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ ድኛለሁኝና ፡ (አምላኬ)
በላይ ፡ በላዩ ፡ ላይ ፡ ልደርብ ፡ ምሥጋና ፡ (አምላኬ)
ኧረ ፡ እኔ ፡ አመለጥኩኝ ፡ አንተን ፡ በማመኔ ፡ (አምላኬ)
በሰውነቴ ፡ ላይ ፡ ታወቀኝ ፡ መዳኔ ፡ (አምላኬ)
ታድያ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ይላል ፡ የተደረገለት ፡ (አምላኬ)
በድግድግ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ የሆንክለት ፡ (አምላኬ)
አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x)
አንተን ፡ በመምረጤ ፡ አላፈርኩም ፡ ከቶ
ሰላም ፡ ሆኖልኛል ፡ ቃልህ ፡ ልቤ ፡ ገብቶ
መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ኮርቼብሃለሁ
በሕይወቴ ፡ ዘምን ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ
አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x)
ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x)
ስገጅ ፡ ስገጅ ፡ አለኝ ፡ ተገርፈሃልና ፡ (አምላኬ)
ልሰጥ ፡ የሚገባኝ ፡ ይኸው ፡ የእጅ ፡ መንሻ ፡ (አምላኬ)
ግሩም ፡ የዕርቅ ፡ ቀን ፡ ስለሆነ ፡ ለእኔ ፡ (አምላኬ)
ምሥጋናዬ ፡ ኢኸው ፡ ይፈሳል ፡ ከልቤ ፡ (አምላኬ)
ከጻድቃን ፡ ማህበር ፡ እኔም ፡ ልቀላቀል ፡ (አምላኬ)
ለዚህ ፡ በቅቻለሁ ፡ ለክብር ፡ ልታሰብ ፡ (አምላኬ)
አዝ፦ አምላኬ ፡ (አምላኬ) ፣ አምላኬ ፡ (አምላኬ) (፫x)
ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፫x)
|