አባቴ (Abatie) - ሶፊያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሶፊያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 2.jpg


(2)

ስማ ፡ በለው
(Sema Belew)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፊያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ
ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

ይሁንልኝ ፡ ብዬ ፡ የተሟገትኳቸው
ባለፈው ፡ ዘመኔ ፡ ኧረ ፡ ብዙ ፡ ናቸው
ጊዜ ፡ ፈጀሁ ፡ እንጂ ፡ ከወዲህ ፡ ከወዲያ
ምን ፡ ጥልቅ ፡ አስብሎኝ ፡ ደርሶ ፡ በአንተ ፡ ሞያ

ትክክል ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ በሥራህ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ
አንተ ፡ አትታረምም ፡ እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ተብለህ

መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ
ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

እንደው ፡ መጨነቄ ፡ ሁሉ ፡ ከልኩ ፡ አያልፍ
አንዳችም ፡ ላልጨምር ፡ አንዳችም ፡ ላላተርፍ
ባይገቡኝም ፡ እንኳን ፡ መንገዶቼ ፡ ሁሉ
ለአንተ ፡ ግን ፡ አባቴ ፡ ጠርተው ፡ ይታያሉ

ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ከሆነልኝ
እንዳረከኝ ፡ ልሁን ፡ የእኔስ ፡ ይቅርብኝ

እኔ ፡ ያልኩት ፡ አልሆነም ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ አልቀረም
አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ
ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም
አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ
ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም (፪x)

እግሮቼን ፡ ከወጥመድ ፡ ማነው ፡ ያወጣቸው
ዓይኖቼ ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ናቸው
በመረጥከው ፡ መንገድ ፡ አስተምረኸኛል
ለማያልፈው ፡ ሕይወት ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል
ለማያልፈው ፡ መብል ፡ መስራት ፡ ይሻለኛል

መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ አንተም ፡ ልጄን ፡ ብለህ
ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

እኔ ፡ ያልኩት ፡ አልሆነም ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ አልቀረም
አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ
ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም
አሁንም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ ፈቃድህ ፡ ያግኘኝ
ስኖር ፡ በዚች ፡ ዓለም (፪x)

ትክክል ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ በሥራህ ፡ ጻድቅ ፡ ነህ
አንተ ፡ አትታረምም ፡ እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ተብለህ (፪x)