From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ለቀብር ፡ ሲዘጋጅ ፡ ሰው ፡ ሬሳ ፡ ተብሎ
ትንሳኤ ፡ ሲሰጠው ፡ ሕይወት ፡ ተቀጥሎ
አንዳች ፡ እጣ ፡ ካሌበት ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ብቃቱ
ሙታንን ፡ ላስነሳ ፡ ክብር ፡ ይሁንለቱ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ
በሽታን ፡ ከሕዝቡ ፡ ደዌን ፡ ለፈወሰ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ተዓምራትን ፡ በእጁ ፡ ሲሰራ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ
አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ
አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ (፫x)
ጠላቶቼን ፡ እንደገለባ ፡ ሲያቃጥላቸው
በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ
የክፋቱ ፡ ሸንጐ ፡ በዘንዶ ፡ ሲመራ
ተገርስሶ ፡ ወድቆ ፡ ክቡር ፡ ሥም ፡ ሲጠራ
ደጋግመን ፡ ሰምተናል ፡ ተቃጥለናል ፡ ሲሉ
ነግቶለት ፡ ሲቦርቅ ፡ የመሸበት ፡ ሁሉ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ
በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ
የቃሉን ፡ እምነት ፡ ለሕዝቡ ፡ አስተማረ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር
በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ
ወንጌልን ፡ ለትውልድ ፡ ለዓለም ፡ ሰበከ
ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር
ለአያሌ ፡ ዘመዓት ፡ ህመም ፡ ያሰቃዩ
በባለ ፡ መድኃኒት ፡ መፍትሄ ፡ አላገኙ
ደዊው ፡ ተፈወሰ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ
ቀምበሩ ፡ ተሰብሮ ፡ ፍፁም ፡ ነጻ ፡ ወጥቶ
ሃኩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)
በሽታውን ፡ ያዳነው ፡ ሃኪሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሃኩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)
በሽታውን ፡ ያዳነው ፡ ሃኪሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x)
ተዓምራትን ፡ በእጁ ፡ ሲሰራ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ
አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ
አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ (፫x)
ጠላቶቼን ፡ እንደገለባ ፡ ሲያቃጥላቸው
በአይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ
|