ፍጠንልኝ (Fetenelegn) - ሶፍያ ፡ ሽባባው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሶፍያ ፡ ሽባባው
(Sofia Shibabaw)

Sofia Shibabaw 3.jpg


(3)

ፍጠንልኝ
(Fetenelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሶፍያ ፡ ሽባባው ፡ አልበሞች
(Albums by Sofia Shibabaw)

ፊትህን ፡ የሚሹ ፡ በእኔ ፡ አይነወሩ
ተስፋ ፡ የሚያደርጉህ ፡ አይተውኝ ፡ አይፈሩ
በምሕረትህ ፡ ፊትህ ፡ አርግልኝ ፡ ጌታዬ
ጉብኝትህ ፡ ይፍጠን ፡ በቤትህ ፡ በአገሬ

ፍጠንልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ፍጠንልኝ
እንደምሕረትህ ፡ ብዛት ፡ ፍረድልኝ
ፍጠንልኝ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ፍጠንልኝ
እንደኃጢአቴ ፡ ከቶ ፡ አታርግብኝ (፪x)

አቤቱ ፡ ልቤ ፡ ጨከነ (፬x)
እግዚአብሔር ፡ አለቴ ፡ ኃይሌ ፡ ነው ፡ እያለ
ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ
ልቤ ፡ ጨከነ

አቤቱ ፡ ልቤ ፡ ጽኑ ፡ ነው (፬x)
ባምላኬ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይሌን ፡ አድሳለሁ
ሰው ፡ ምን ፡ ያደርገኛል ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ልቡ ፡ ጹኑ ፡ ነው